Lyrics

ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ኦሆ ፡ የምትቀርበኝ እንደ ፡ ዓይንህ ፡ ብሌን ፡ ኦሆ ፡ የምጠብቀኝ ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ብዬ ፡ ኦሆ ፡ የቆዘምኩ ፡ ለታ ፍቅርህ ፡ ይሰማኛል ፡ ኦሆ ፡ አልፏ ፡ የእኔን ፡ ሁኔታ በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ፡ ሀሌሉያ ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ ኦሆሆሆሆሆ ፡ ላምልክ (፰x) አይደክመኝም ፡ በቃ ፡ አምልኬ ፡ አምልኬ ፡ ልብህ ፡ እስኪረካ የኔንም ፡ መስዋእት ፡ የፃፍኩትን ፡ መዝሙር ፡ ወደኀዋል ፡ ለካ የቀረው ፡ ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ በፊትህ አንተን ፡ እያመለኩኝ ፡ እያከበርኩህ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላምልክ (፪x) ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ላምልክህ ውለታህን ፡ ሳስበው ፡ መግለጫ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ ፡ አዎ ያንትን ፡ ፍቅር ፡ ሳስብ ፡ መግለጫ ፡ ቃላት ፡ አጣሁ ፡ አዎ በጨለማው ፡ ሀገር ፡ ኦሆ ፡ ሀጥያት ፡ ክብዶብኝ ማነው ፡ ከዚህ ፡ ስቃይ ፡ ኦሆ ፡ የሚያሳርፈኝ በሞት ፡ ተከብቤ ፡ ኦሆ ፡ ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ሳለ በፍቅርህ ፡ አድነህ ፡ ኦሆ ፡ ታሪኬን ፡ ለወጥከው በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ፡ ሀሌሉያ ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ በልቤ ፡ ፅላት ፡ ላይ ፡ ያረፈው ፡ ፍቅርህ ይቀሰቅሰኛል ፡ ሁሌ ፡ እንዳመልክህ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out