Lyrics

የእግዚያብሔር ፡ ግርማ ፡ ክብርና ፡ ሞገሱ በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ታይቶ ፡ ያወራል ፡ ስለእርሱ ፍቅሩ ፡ ርህራሄው ፡ ቸርነት ፡ ምሕረቱ ሁሉም ፡ ይዘምራል ፡ በዜማ ፡ አንደበቱ ሁሉን ፡ ቻይነቱ ሳይሆን ፡ ገና ፡ ሰማይ ፡ ሳይሆን ፡ ገና ፡ ምድር መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር በላይ ፡ እና ፡ በታች ፡ የሚባል ፡ ሳይኖር አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር ሳትታይ ፡ ጨረቃ ፡ ሳትበራ ፡ ፀሐይ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ቀድሞ ፡ አልነበረ ፡ ወይ ጥዋት ፡ እና ፡ ማታ ፡ ተብሎም ፡ ሳይለይ በሥልጣን ፡ በክብር ፡ እርሱ ፡ አልነበር ፡ ወይ አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x) ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚኖረው ሕያው ፡ አምላክ ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር የሰራችሁ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ በመገዛት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉ (፪x) የውሃው ፡ ክምችት ፡ ሳይባል ፡ ባሕር መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር ምድርም ፡ ሳታበቅ ፡ ቡቃያና ፡ ሳር አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር ሳይለዩ ፡ ገና ፡ ውሃና ፡ መሬቱ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በኃይል ፡ በችሎቱ እለታት ፡ ዓመታት ፡ ዘመናት ፡ ሳይሆኑ እርሱ ፡ እንዳለ ፡ አለ ፡ በክብር ፡ ዙፋኑ አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x) ሳይሰራ ፡ አዳም ፡ ሳትመጣ ፡ ሄዋን መጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር እፍ ፡ ሳይልበት ፡ ገና ፡ እስትንፋሱን አስቀድሞ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነበር ሳይባሉ ፡ ገና ፡ ብዙ ፡ እና ፡ ተባዙ ምድርን ፡ አስተዳድሩ ፡ ፍጥረታትን ፡ ግዙ አዳም ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ሳይመላለስ በማደሪያው ፡ አለ ፡ የክብር ፡ ንጉሥ ስሙም ፡ ቅዱስ አዝ፦ በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር ፡ በመጀመሪያ በመጀመሪያ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ በመጀመሪያ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እግዚአብሔር ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ነበር ፡ እርሱ ፡ መጀመሪያ ፡ ሃሌሉያ (፪x) ለነበረው ፡ ላለው ፡ ለሚኖረው ሕያው ፡ አምላክ ፡ ልዑል ፡ እግዚአብሔር የሰራችሁ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ በመገዛት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉ (፪x)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out