Featured In

Lyrics

በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ በክብርና ፡ በግርማው ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው እግሮቹ ፡ በደመናት ፡ ላይ ፡ ይራመዳሉ ዓይኖቹ ፡ በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ ፡ ያያሉ አይገለጥም ፡ በቋንቋ ፡ ታላቅነቱ እኔ ፡ ክብር ፡ እሰጣለው ፡ ለጌትነቱ አይገለጥም ፡ በቋንቋ ፡ ታላቅነቱ እኔ ፡ ስግደት ፡ አበዛለው ፡ ለጌትነቱ ፍጥረት ፡ የሚሰማው ፡ የሚወደው ገና ፡ ሳይነጋ ፡ በማለዳው እግዚአብዜር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ የሚለውን ፡ ቃል ፡ በመሆኑ እኔም ፡ ልዘምር ፡ ይህንኑ እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በዙፋኑ እኔም ፡ ልዘምር ፡ ይህንኑ አምላኬ ፡ አለ ፡ በዙፋኑ በክብር ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ከብሯል በኃይል ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ኃይሏል ፡ በሥልጣን ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ተሹሟል በሞገስ ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ደምቋል ፡ በዝና ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ታውቋል ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቃል ፭ ማደሪያው ፡ የተለየ ፡ ነው ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ ለዘለዓለም ፡ የሚኖር ፡ በሙሉ ፡ ኃይሉ ባለግርማና ፡ ሞገስ ፡ የክብር ፡ ጌታ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ዕልልታ ባለግርማና ፡ ሞገስ ፡ የክብር ፡ ጌታ ምሥጋና ፡ ክብር ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ዕልልታ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ በክብርና ፡ በግርማው ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው በክብር ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ከብሯል በኃይል ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ኃይሏል ፡ በሥልጣን ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ተሹሟል በሞገስ ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ደምቋል ፡ በዝና ፡ ማን ፡ እንደርሱ ፡ ታውቋል ፡ ኢየሱስ ፡ ከሁሉም ፡ ይልቃል ፭ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ በማደሪያው ፡ ላይ በክብርና ፡ በግርማው ሳይለዋወጥ ፡ ሳይነዋወጥ እንዲሁ ፡ እንደጵና ፡ ያለው ከነችሎቱ ፡ ከነብርታቱ ፡ የሚኖረው ኧረ ፡ ይሄ ፡ ማነው የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው
Lyrics powered by www.musixmatch.com
Get up to 2 months free of Apple Music
instagramSharePathic_arrow_out