Lyrics

ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ከኔ ጋር ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር ጠላቶቼ በቁጣቸው ብዛት ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር ግን እግዚአብሔር ምህረትን አበዛ አሻገረኝ መንገድ አበጀና አሻገረኝ መንገድ አበጀና ይኸው ዛሬ በህይወት ቆሚያለሁ በብዙ ድል በብዙ ምስጋና በብዙ ድል በብዙ ምስጋና ተጠነቀቀልኝ ጌታዬ ተጠነቀቀልኝ ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ ከጃቸው ሚያስጥል እንደሌለ እጅግ የበረቱ መሰሉ አላስተዋሉትም ነበረ ከኔ ጋር ያለውን እረኛ ድካም ከቶ እንደማያውቀው እኔን ለማዳን እንደማይተኛ ስላለ ግን ጌታ ከጎኔ ስላል እርሱ ካጠገቤ በጠላቴ ፉከራ ዛቻ ስጋት አይገባውም ይህ ልቤ ተማምኜ በርሱ ተማምኜ በትከሻው መሃል አድራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ሰላም ነው ሁሉ ሰላም ነዉ ጌታ ነው ከጎኔ ያለዉ ደህና ነው ሁሉ ደህና ነዉ ጌታ ነው በቤቴ ያለዉ የላባ ቀንበር ቢከብደበት በቸገር ቢጠማ ቢከፋ አመልጣለሁ ብሎ ቢያስብም ማልዶ ቢኮበልል ቢጠፋ ተከታተለዉ ደረሰበት በቁጣው ሊያጠፋውም ዝቶ የወደደውንም እንዲያደርግ በእጁ በሃይሉ ተመክቶ የያቆብ አምላክ ቀደመ ለላባ በህልም ነገረው እንክዋን ልትጎዳ ልታጠፋው በክፉ ቃል አትናገረው በማስጠንቀቂያ ቃል ገስጾ ሃሳብ እቅዱን አፈረሰ ያሳዳጁን ዛቻ ላልሰማው ለባሪያው ለያቆብ ደረሰ ሰላም ነው ሁሉ ሰላም ነዉ ጌታ ነው ከጎኔ ያለዉ ደህና ነው ሁሉ ደህና ነዉ ጌታ ነው በቤቴ ያለዉ ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ከኔ ጋር ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር ጠላቶቼ በቁጣቸው ብዛት ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር ግን እግዚአብሔር ምህረትን አበዛ አሻገረኝ መንገድ አበጀና አሻገረኝ መንገድ አበጀና ይኸው ዛሬ በህይወት ቆሚያለሁ በብዙ ድል በብዙ ምስጋና በብዙ ድል በብዙ ምስጋና ተጠነቀቀልኝ ጌታዬ ተጠነቀቀልኝ ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው ለኔ ጨለማው መንገዴን እንዳይዘጋ ፍርሃት ስጋት ሁሉ ቀረ በልጁ ወደርሱ ስጠጋ ተሰነካክዬ እንዳልቀር ህይወቴም እንዳትሆን ከንቱ እንዳልሆንበት መሳለቂያ ገነነልኝ ለኔስ ምህረቱ ስላለ ግን ጌታ ከጎኔ ስላል እርሱ ካጠገቤ በጠላቴ ፉከራ ዛቻ ስጋት አይገባውም ይህ ልቤ ተማምኜ በርሱ ተማምኜ በትከሻው መሃል አድራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out