Music Video

በስምህ ውስጥ Azeb Hailu አዜብ ሀይሉ - Live Concert "Dink Sitota"
Watch {trackName} music video by {artistName}

Featured In

Lyrics

በስምህ ውስጥ ሃይል አለ በስምህ ውስጥ ሞገስ በስምህ ውስጥ ድል አለ በስምህ ውስጥ ፈውስ በስምህ ውስጥ ሃይል አለ በስምህ ውስጥ ሞገስ በስምህ ውስጥ ድል አለ በስምህ ውስጥ ፈውስ የጸና ግምብ ነው ስምህ የጻድቅ መሸሻ ከዚህ ዓለም ግብግብ መሸሸጊያ ዋሻ ከድካም ህመሜ የምፈወስበት ኢየሱስ ያንተ ስም መድሃኒት አለበት ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሄር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ ስምህ ማንነትህ ማንነትህ ስምህ እንደተጠራህበት እንደዚያው መሆንህ አዳኝ ሲሉህ አዳኝ ነህ ህይወት ሲሉህ ህይወት ኢየሱስ ያንተ ስም እውነተኛ እውነት ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሄር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃናዊ አብሪ ስም አለህ በሰልፉ ሜዳ ላይ በውጊያው መንደር ስምህ የጦር እቃችን የማይበገር የልጆችህ አንገት ቀና የሚልበት ኢየሱስ ያንተ ስም ታላቅ ሃይል አለበት
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out