Lyrics

ስለበዛልኝ ምህረቱ ስለደገፈኝ ፀጋው መቋጫ ከቶ አጣሁኝ ሳወራው ቢመሽ ቢነጋ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የበጐ ነገር መገኛ የሆነው ጌታ እግዚአብሔር እርሱ ነው የኔ እረኛ ስለበዛልኝ ምህረቱ ስለደገፈኝ ፀጋው መቋጫ ከቶ አጣሁኝ ስዘምር ቢመሽ ቢነጋ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የበጐ ነገር መገኛ የሆነው ጌታ ኢየሱስ እርሱ ነው የኔ እረኛ እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) በምድር ላለው ህይወቴ ከእናቴ ማህፀን ጀምሮ መች ያልቃል የርሱ ቸርነት ተዘርዝሮና ተነግሮ አምላኬ ለኔ ያረገው ባወራው ከቁጥር በዛ ልዘምር እንጂ ሳልሰለች ሳልቆጥበው እንደ ዋዛ እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) አጥኖ ፀሃይን ሞቆ የአንተን ምስጋና ካወራ ምህረትህን ያየሁ እኔ እኔማ እንዴት አላወራ በልጅህ የአንተ ልጅ ሆኜ ገብቼ ደጅህ ተከፍቶልኝ ያየሁት እና የቀመስኩት የምለው ብዙ ነገር አለኝ እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪) ሙሉ ሆኖ እንደሚፈስ እንደ ውሀ ነው ሰላሜ በክርስቶስ ባገኘሁት የህይወት ቃል ነው መለምለሜ ከማይነጥፍ ከማይደርቀው የህይወት ምንጭ ተጠግቼ የዚህን አለም በረሃ የድርቅ ወሬ መች ፈርቼ እረኛዬ የነፍሴ መሰማሪያ እረኛዬ መዋያዬና ማደሪያ እረኛዬ እርሱ ነው የኔ መኖሪያ (፪)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out