Lyrics

በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና (፫) እንደወራጅ ፡ ዉሃ ፡ ልክ ፡ እንደጅረቱ አይቋረጥብህ ፡ አምልኮዬ ፡ ፊቱ ይፍሰስ ፡ በማለዳው ፡ ይፍሰስ ፡ በሌሊቱ መሳይ ፡ ስለሌለው ፡ ጌታ ፡ ጌትነቱ (፪) ላምልከው ፡ በአምልኮዬ ፡ ላክብረው ፡ በዝማሬዬ ላግንነው ፡ በዕልልታዬ ፡ ላድምቀው ፡ በጭብጨባዬ ይገባዋል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬) የመውደዴን ፡ ልኩን ፡ የፍቅሬን ፡ መግልጫ ካለኝ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ የምሰጠው ፡ ብልጫ ለሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ለነፍሴ ፡ ንጉሥ አለኝ ፡ የምሰዋው ፡ ከነፍሴ ፡ የሚፈስ የቅኔው ፡ የዜማ ፡ ሽታ ፡ ታጅቦ ፡ በብዙ ፡ ቦታ ከምድር ፡ ይውጣ ፡ ያስተጋባ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ማደሪያ ፡ ይግባ ይገባሃል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬) በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና (፫)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out