Lyrics

የፍቅርህ ምርኮኛ እኔ ሆኛለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ የፍቅርህ ምርኮኛ ባንተ ዘንድ ያለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ እወድሃለሁ ። በበደሌ ሞቼ ሳለሁኝ ለሰይጣን እየተገዛሁ የቁጣ ልጅ ሆኜ ነበር ያ ሁሉ ታሪክ ሆኖ ቀረ በቀራኒዮ ዉዴ ተሰቅሎ ፃድቅ አረገኝ እየሱስ በኔ ቦታ ሆኖ በቀራኒዮ ዉዴ ተሰቅሎ ፃድቅ አረገኝ እየሱስ በኔ ቦታ ሆኖ የፍቅርህ ምርኮኛ እኔ ሆኛለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ የፍቅርህ ምርኮኛ ባንተ ዘንድ ያለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ እወድሃለሁ ። እንደ ባርያ ስኖር ሳለሁ ለሀጢያት እያጎበደድኩ ቀንበር በላዬ ተጭኖብኝ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነበርሁኝ አሁን ግን ልጅነኝ የእግዚአብሔር ወራሽ ተወልጃለሁ ከመንፈሱ ሆንኩኝ አዲስ ፍጥረት አሁን ግን ልጅነኝ የእግዚአብሔር ወራሽ ተወልጃለሁ ከመንፈሱ ሆንኩኝ አዲስ ፍጥረት የፍቅርህ ምርኮኛ እኔ ሆኛለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ የፍቅርህ ምርኮኛ ባንተ ዘንድ ያለሁ ደግሜ ደግሜ ወድሃለሁ እወድሃለሁ ። ጠፍቼ ስኖር ካንተ ርቄ ኮብልዬ ያንተን ፍቅር ንቄ የስጋ ምኞቴን ስከተል ከእግዚአብሔር ተጣልቼ ነበር ደግሞ እንደገና የእንደገናዬ በትንሳኤ ሀይል አዲስ ሰው አረግከኝ ጌታዬ ደግሞ እንደገና የእንደገናዬ በትንሳኤ ሀይል አዲስ ሰው አረግከኝ ጌታዬ ኢየሱስ ገና እወድሃለሁ በሞትህ ሞቴን ስለሻርከው ኢየሱስ ገና አፈቅርሃለሁ በአብ ቀኝ በአንተ ውስጥ ስላለሁ ኢየሱስ ገና እወድሃለሁ በሞትህ ሞቴን ስለሻርከው ኢየሱስ ገና አፈቅርሃለሁ በአብ ቀኝ በአንተ ውስጥ ስላለሁ እወድሃለሁ ።
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out