Lyrics

ለካ ለካ አልተያየንም ለካ አልተደማመጥንም ለካ ሌቱን አሳልፈን ለካ ቀን አብረን አልዋልንም ለካ ለካ በድናችን ነው ለካ የሸክላ ቋቋታ አቤት ያሁሉ ሳቅ ስላቅ ያ ያሁሉ ጨዋታ ምነው የጋለውን ፍቅር ውሃ ደፋሽበት አንቺስ ማስመሰሉን እንጂ መሆኑን አታውቂበት ለካ ለካ በእድሚያችን ነው ለካ የያዝነው ጨዋታ ወትሮስ መች ይመጣል ብለሽ ወትሮስ ያለፍቅር ደስታ ለካ ሁካታ ነበር ለካ የገደል ማሚቶ በቃ የፍቅራችን ልሳን በቃ ቀረ ተስተጋብቶ ዘመናዊነቱ የጊዜው ስጦታ ጥርስ መክፈት ሆኖ መላቅ በፈገግታ መገመቴን ሳላውቅ ለስሌት መቅረቤን ስደምር ስቀንስ ሳባዛው ሀሳቤን እንደው ላይሆንልኝ አደከምኩት ልቤን ዘመናዊነቱ የጊዜው ስጦታ ጥርስ መክፈት ሆኖ መላቅ በፈገግታ መገመቴን ሳላውቅ ለስሌት መቅረቤን ስደምር ስቀንስ ሳባዛው ሀሳቤን እንደው ላይሆንልኝ አደከምኩት ልቤን ለካ አልተያየንም ለካ አልተደማመጥንም ለካ ሌቱን አሳልፈን ለካ ቀኑን አብረን አልዋልንም ለካ ለካ በድናችን ነው ለካ የሸክላ ቋቋታ አቤት ያ ሁሉ ሳቅ ስላቅ ያ ሁሉ ጨዋታ ለካ ለካ አልተያየንም ለካ አልተደማመጥንም ለካ ሌቱን አሳልፈን ለካ ቀን አብረን አልዋልንም ለካ ለካ በድናችን ነው ለካ የሸክላ ቋቋታ አቤት ያሁሉ ሳቅ ስላቅ ያ ያሁሉ ጨዋታ ምነው የጋለውን ፍቅር ውሃ ደፋሽበት አንቺስ ማስመሰሉን እንጂ መሆኑን አታውቂበት ለካ ለካ በእድሚያችን ነው ለካ የያዝነው ጨዋታ ወትሮስ መች ይመጣል ብለሽ ወትሮስ ያለፍቅር ደስታ ለካ ሁካታ ነበር ለካ የገደል ማሚቶ በቃ የፍቅራችን ልሳን በቃ ቀረ ተስተጋብቶ እይው ባ'ንድ ልቤ እይው ስደላደል እንግዲህ ይቆጭሽ የሰራሽው በደል እኔማ አልታመም አንቺም አትሙቺና ለወቀሳ ያብቃን ሁሉም ይለፍና አሁን አይመችም መች ተያየንና እይው ባ'ንድ ልቤ እይው ስደላደል እንግዲህ ይቆጭሽ የሰራሽው በደል እኔማ አልታመም አንቺም አንቺም አትሙቺና ለወቀሳ ያብቃን ሁሉም ይለፍና አሁን አይመችም መች ተያየንና ለካ አልተያየንም ለካ አልተደማመጥንም ለካ ሌቱን አሳልፈን ለካ ቀኑን አብረን አልዋልንም ለካ ለካ በድናችን ነው ለካ የሸክላ ቋቋታ አቤት ያ ሁሉ ሳቅ ስላቅ ያ ሁሉ ጨዋታ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out