Lyrics

ችዬው ኖሬ ነበር የውስጤን አምቄ ከንግዲስ አልችልም ሚስጥሬን ደብቄ እየዋለ ሲያድር ባሰብኝ ጭንቀቴ እስቲ መላ በይኝ እርጂኝ አብሮ አድጌ የሆድሽን በሆድሽ ይዘሽው በሚስጥር ጉዳዩን ሳትነግሪኝ ምኑን ልስጥሽ ምክር አውጥተው ከሰው ጋር ካልተወያዩበት ውስጥ ውስጡን ይጎዳል ሀሳብና ጭንቀት እንቅልፍ አሳጥቶ እንዲ ሚያስጨንቅሽ ምን ይሆን ሚስጥሩ እስኪ ልጠይቅሽ ብትነግሪኝስ? ፈርቼሽ ነው በይ አጫውቺኝ ኧረ አይጣል ነው ምን ገጠመሽ? ዱብ እዳ ነው የምን እዳ? ፈተና ነው ብትነግሪኝስ? ፈርቼሽ ነው በይ አጫውቺኝ ኧረ አይጣል ነው ምን ገጠመሽ? ዱብ እዳ ነው የምን እዳ? ፈተና ነው አይኔ እየናፈቀ ልቤ እያፈቀረ አለሁ እስከዛሬ መውደዴን ሳልነግረው እንደምን ልንገረው እኔው አፍ አውጥቼ የባህል ልማዱን የሴት ወጉን ትቼ አዲስ ነገር አይደል ሚደርስ ባንቺ ብቻ ባንድ እጅ አጨብጭቦ ባንድ በሬ ስቦ መች ይሆናል ብለሽ አንድ ሰው አስቦ ምላሹን ላታውቂ ብቻሽን ብትወጂው የጋራ ነው ፍቅር ሁሉንም አስረጂው አታስቢ ፍቅር እኮ ነው በይ ንገሪው ፈርቼው ነው አስረጂዋ ምን ልበለው? ምን ይሻላል? ኧረ አይጣል ነው አታስቢ ፍቅር እኮ ነው በይ ንገሪው ፈርቼው ነው አስረጂዋ ምን ልበለው? ምን ይሻላል? ኧረ አይጣል ነው
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out