Lyrics

Ahadu ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ታወቀብኝ እሷን መውደዴ ወይ ጉዷ(ወይ ጉዷ) ወይ ጉዷ (ወይ ጉዷ) አይቀርም አንድ ቀን መውደዷ ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ታወቀብኝ እሷን መውደዴ ወይ ጉዷ(ወይ ጉዷ) ወይ ጉዷ (ወይ ጉዷ) አይቀርም አንድ ቀን መውደዷ የሺ ውበት ሀረግ በውበት አንደኛ ሁሉን ያማለለች የልቤ ጋደኛ ያጨኋት አድርጌ የራሴ ዘውድ ለኔ እሷ ናት የኔማ የኔ ቁምነገሬ ባትመቸኝ ህይወት ሆናብኝ ተራራ ታሳልፈኛለች ችግሬን አባራ ባዝን መከታዬ ብደሰት ደስታዬ እኔ ምሞትላት የኔ ግራ ጎኔ የአካሌ ክፋይ ምንጊዜም ምወዳት በህልሜም በዕውኔም ሁሌ የማወሳት ከሌሎቹ ሴቶች ለየት አድርጎ የሰራት ከየትኛውም ቦታ እንከን ማይወጣላት ውበት ብቻ አይደለም እሱ የለገሳት የኔ የሺ ሀረግ ፀባየ ሠናይ ናት ሙሉ ልቤን ለሰጠኋት አንዷን ህይወቴን ላካፈልካት ዛሬም ነገም የማፈቅራት እሷ ለኔ አንደኛ ናት ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ታወቀብኝ እሷን መውደዴ ወይ ጉዷ(ወይ ጉዷ) ወይ ጉዷ (ወይ ጉዷ) አይቀርም አንድ ቀን መውደዷ ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ወይ ጉዴ(ወይ ጉዴ) ታወቀብኝ እሷን መውደዴ ወይ ጉዷ(ወይ ጉዷ) ወይ ጉዷ (ወይ ጉዷ) አይቀርም አንድ ቀን መውደዷ በርግጥ ቆንጆ ናት ምንም አይወጣላት ከመልክ ከቁመና አማልቶ የሰጣት ከፊትም ከኋላ ከታች እስከ ላይ ገዳይ ናት ልጅቷ ቆንጆ አማላይ በዚህ ቁንጅና ላይ ቆንጂት ትዘልፋለች በውበቷ አስራ ልቤን ወስዳዋለች ማን ነው ተጠያቂ ቆንጆ የሚቀጣ መተንፈስ አቃተኝ አ ልቤ ላይ ተቀምጣ ተይ በሏት ተይ በሏት ቆንጅዬን ተይ በሏት መፀፀት ነው ትርፉ በኋላ ብሞትባት ምንድን ነው ምንድን ነው ምንድን ነው ኩራቱ ከልኩ ካለፈ ወጉ ሴትነቱ ዋጋ ያስከፍላል ወዳጅን መግፋቱ በይ ነይ ወደኔ ኩራቱን ተይና ኩራቱን ተይና ያቡዬ በይና(ያቡዬ በይና) ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ አለ እሷም ጋ እኔን መፈለጉ ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ ኩራቷ ነው የሴትነት ወጉ አለ እሷም ጋ እኔን መፈለጉ(let's go) ኩራቷ ኩራቷ ኩራቷ ውበቷ ኩራቷ ኩራቷ ኩራቷ ውበቷ ኩራቷ ኩራቷ ኩራቷ ውበቷ ኩራቷ ኩራቷ ኩራቷ ውበቷ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out