Lyrics

ሰባራ ህልም አለችኝ ልፋት የሰበራት ነፋስ ማዕበሉ ውሃው ሲያንገላታት ተጥላ እንዳትቀር መልሼ አዋቀርኳት ደግማ እንዳታፈስ በቅጥራን ለበጥኳት አሻግሬ እያየው ጀልባዬን ጠገንኳት ታደርስ ይሆን ብዬ ብዙ ለፋሁባት ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ድካሙ ብጫነኝ ስራዬን እንዳልቀጥል ዋርካው ስር አሸለብኩ ወገቤን ላሳርፍ ትንሽ እንደቆየ የምስራቅ ነፋስ መጥቶ ጀልባዬን ወሰዳት በወንዙ ታግዞ ውሃው ቢያንሳፍፋት ስቃ ጥላኝ ሄደች በአውራቂሱ ነፋስ እየተደሰተች ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ በከንቱ ደከምኩኝ ምንም ላትፈይድ ጊዜዬን ፈጀሁት የትም ለማትደርስ ቁጭት ከንዴት ጋር ተባብረው ቢያፍኑኝ ከሚታየኝ ቅዠት ድንገት አባነኑኝ ዓይኔን ከሰመመን ታግዬ ብገልጥ ጀልባዬን አየሗት ወንዙን ስትታገል ነፋስ ቢደልላት ይዟት ሊኮበልል "አልሄድም" አለችው ጥላኝ ላትሻገር ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ ትንሿ ጀልባዬ
Writer(s): Dawit Cherent Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out