Music Video

Hana Tekle - Selam New (ሰላም ነው) Lyrics Video
Watch {trackName} music video by {artistName}

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Hanna Tekle Sarhe
Hanna Tekle Sarhe
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Hanna Tekle Sarhe
Hanna Tekle Sarhe
Songwriter

Lyrics

መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ የአባቶቼ የነ ሙሴ አባት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም ብታድነኝም ባታድነኝም አንተ መልካም ነህ ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ ለአደራረግህ ማስተካከያ ከማንም አትሻም ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም ያስጨነቀኝ ቀንበሬ ውስጤን አንቆ የያዘው ለኔ እንጂ ቢከብደኝ ኢየሱስዬ ላንተ እንዴት እንዲህ ቀላል ነው የዛሬው ድቅድቅ ሌሊቴ ይገባሃል ሚስጥሩ ፊትህን እያየሁ ዛሬም ግን እላለሁ ሰላም ነው ሰላም ነው እላለሁ በእጅህ የገባውን ነገሬን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ ውስጤ ሸክም አዝሎ እጅህን እያየሁ አልገባሽ ቢለኝ ነገሩ ማዕበል ወጀቡን ፈርቼ ውስጤን ብርዱ ተሰማኝ ሰው ነኝና ሰግቼ ጉልበቴ እልሃለሁ ዛሬም አቅሜ አንተ ነህ አቤቱ እምነቴ እንደው አልታመነም አይተኸኝል በብዙ ግን እላለሁ ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝን ትላንትን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ በዚህ አይቀጥልም ክብርህን አያለሁ ሰላም ነው እላለሁ ያደረክልኝን ትላንትን እያየሁ ሰላም ነው እላለሁ ይህም ሌሊት ያልፋል ክብርህን አያለሁ ደህና ነው ካለች ሱናማዊቷ የአንድ ልጇን ነፍስ አጥታው ከቤቷ ታዲያ እንዴት አልል ሰላም ነው ባለቤት አለኝ የኔ አይደለሁም በትንሽ ትልቁ ብዙ ጭንቀቴ መልስ እንዳይሆነኝ ለዘመመው ቤቴ ተረድቻለሁ ይህን አውቂያለው ነገሬን ሁሉ አስረክቤዋለው መኖሪያዬ የዘላለም አምላክ የአባቶቼ የነ ሙሴ አባት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም የሚያውቅልኝ እንደ አንተ አላገኝም ብታድነኝም ባታድነኝም አንተ መልካም ነህ ይህንን አድርግ ያንን አታድርግ መች ትባላለህ ለአደራረግህ ማስተካከያ ከማንም አትሻም ፍፁም በስራህ ፍፁም በምክርህ አትሳሳትም ሰላም ነው (×፰) አውጃለሁ ዛሬም መልካምነትህን ባልሞላው ነገሬ ስንፍናን አልሰብክም እምነቴን አልጥልም ከንቱ ተናገሬ ከአንተ በላይ ለኔ ለመጪው ዘመኔ እኔ አላውቅምና መቆዘሜን ጥዬ ይህም ያልፋል ብዬ ልለፍ በምስጋና ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ እንድማር ነው አባቴ ንፋሱ ሲያይል ሲበረታ ድንቅህን ላይ ነው የማታ ማታ ብርቱ ሰልፍ ሲሆን ሕይወቴ ለትምህርቴ ነው አባቴ ወጀቡ ቢያይል ቢበረታ ግን ድሉ የኔ ነው የማታ ማታ ሰላም ነው (×፰)
Writer(s): Samuel Alemu, Hanna Tekle Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out