Credits

COMPOSITION & LYRICS
Asnaqetch Werqu
Asnaqetch Werqu
Songwriter

Lyrics

አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ ሳስብህ አድራለሁ አንተን ሳሰላስል ሀሳብ በውለታ ይቆጠር ይመስል አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ አዲሱን ቀሚሴን እሳት ፈጀው ማታ ፍቅሬ ያንተን ነገር ስቋጥር ስፈታ አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ ከማዉጣት ከማውረድ ዘላለም ከማሰብ ላርግህ ከደረቴ እንደ ልሳነ ሰብ አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ አሎድሽም በለኝ ልቤ ተጨነቀ መጥላትም ፍቅር ነው ቁርጡ ከታወቀ አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ ደናደሪ ብሎ እጄን ቢጨብጠው ተበጠስኩኝ ደክር ሟሟሁኝ እንደ ጨው አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ እስቲ ዝም በሉት ሠው ይነጋገራል መጨነቄን አውቆ መቶልኝ ይሆናል አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ አወጣጥህ መልካም ቡቃያህ ማማሩ አንተ አይደለህም ወይ የትዝታ ዘሩ አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ አለም አለም ሸጋ(2*) ቁጭ በል እናውጋ
Writer(s): Asnaqetch Werqu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out