Lyrics

የትዝታዬ እናት የስሜቴ እመቤት የፍላጎቴ ምንጭ የእድሌ ባለቤት የምታስታውሺኝ ያለፍኩትን ደስታ አንቺ ብቻኮ ነሽ የኔ ልብ አለኝታ ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት እህ... እህ... እህ... እህ እህ እህ... እህ አሄ... አህ... አህ የተጫወትነዉን ምንግዜም አልረሳም እንዲህ ተለያይተን በናፍቅት ብከሳም አይከዳሽም ልቤ ሰው መክዳት አያውቅም እስኪለያይ ድረስ ከለቅሶ ከሳቅም ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት እህ... እህ... እህ... እህ እህ እህ... እህ አሄ... አህ... አህ ዉበትሽን እንዳላይ እርቄም ማርኮታል ልቤ ግን ግልፅ ነው ተይ ስሚኝ መዝግቦ ይዞታል ባካል ባላይሽም እሆይ ባሳብ ግስጋሴ አልተነጣጠልንም አዎ ነፍስሽ እና ነፍሴ ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት ያሳለፍነው ዘመን ደስታን ያየንበት ተመልሶ ቢገኝ አሁን ምናለበት እህ... እህ... እህ... እህ እህ እህ... እህ አሄ... አህ... አህ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out