Lyrics

ስትወድ ፡ ብዙ ፡ ስትምር ፡ ብዙ ደግነትህ ፡ አበዛዙ መልካምነትህን ፡ ለእኔ ፡ አልቆጠብከው ለያንዳንዱ ፡ ነገር ፡ አብዝተህ ፡ አየሁ ከለመንኩህ ፡ እና ፡ ካሰብኩት ፡ በላይ ሁሉ ፡ ተከናውኖ ፡ ተደርጎልኝ ፡ ሳይ ምለውን ፡ አጣሁ ፡ ዝም ፡ አሰኘኝ የአንት ፡ ስራ ፡ አስደነቀኝ (፪x) አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x) ኃይሌ ፡ እንዳልል ፡ አይደል ፡ ብዙ ብልጠት ፡ በዝቶ ፡ አልደርስኩ ለእኔ ፡ አንተ ፡ በርትተህ ፡ ተናጥቀህልኛል በርትተህ ፡ ተውግተህ ፡ ምርኮን ፡ በዝብዘሃል እንካ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ላንት ፡ ላብዛ ፡ ላብዛ ሳልጠግብ ፡ ውዳሴህም ፡ አፌን ፡ ከቶ ፡ አልዝጋ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ የምወድህ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ የማበልጥህ (፪x) አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x) ሙት ፡ ነበርሁ ፡ የማረባ ከምንደሬ ፡ ስትገባ ምን ፡ ነበረኝና ፡ ምኔን ፡ ወዶ ፡ ልበል የትኛው ፡ እኔነቴ ፡ ለዚ ፡ ሳበው ፡ ልበል እንዲያው ፡ ቸርነትህ ፡ ያ ፡ ፍቅርህ ፡ ካልሆነ አይገባኝም ፡ መድሃኒቴ ፡ የእኔ ፡ ጌታ የአንተ ፡ ውለታ (፪x) አዝ፦ ከተደረግልኝ ፡ በጎነት ፡ አንዳችም ፡ ለእኔ ፡ ማይገባ ፡ ነበር እንደ ፡ ቸርነትህ ፡ አርገሃልና ፡ እደነቃለሁ አብዝቼ ፡ ተመስገን ፡ እላለሁ (፪x)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out