Lyrics

ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ ድንገት እንደነቃ እንደባነነ ግራ መጋባቴን የሚነግረኝ አንዳንዴም ከራሴ ሳወራ ነው ከውስጤ ሰላም ጋር የሚያኖረኝ ከሰው ጋር እየኖርኩ ሰው ከረሳኝ ውስጤ እንደ ዝምታ ሰሚ ካጣ ታዲያ ለምን ብዬ አወራለው እራሴን በጩኸት እስክቀጣ ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደሆን (ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋው እንደሆን) ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ (ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ) እንደ ቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ ከዚህ አገር ጩኸት ከዚያ አገር ሁካታ አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ ልቤ እስኪ እረጋልቤ አረፍ እንበል ልቤ ውስጤን ለማዳመጥ በዝምታ እስኪ ልሂድ ደሞ ጭር ካለው ቦታ ለልቤ ጓደኛ እራሴው ነኝ ዛሬ ልስጠው ግዜ ላጫውተው ያጫውተኝ የዝምታን ቋንቋ ሰም ወርቁን የዝምታን ጥልቀት ሚስጥር ቃልን ከራሱ የሚያወጋ ሰው ያውቀዋል ነፍሱን ያዳመጠ ልክ እንደ እኔ ታዲያ እኔ መች ሆነ ሰው ጠልቼ ጭር ያለውን ስፍራ ያሶደደኝ የመግባባት እርካብ ጥማት እንጂ የዝምታን መንገድ ያስመረጠኝ ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋኝ እንደሆን (ሰው ባጣ እስኪ ልየው ይከፋው እንደሆን) ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ (ኧረ አንዳንዴም በዝምታ አለ ጨዋታ) እንደ ቀላል እንጂ እንደ ብርቅ እንደ ብርቅ አትቁጠረው ልቤ ተሰፍሮ ላያልቅ ከዚህ አገር ጩኸት ከዚያ አገር ሁካታ አረፍ እንበል ልቤ ጭር ካለው ቦታ
Writer(s): Simone Tsegay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out