Lyrics

ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር በሀገር ተሞ ክብሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ ያለ ፍቅር ከንቱ አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ መውደድ ነው ኩራቱ ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር ሳይጎላብኝ ስሜ ባልባል ጀግና ጌታ ልኑር የትም ቦታ አያርገኝ ኧረ እኔ ታላቁን እስክንድር ባሻኝ እንዳድር የዓለም የፍቅር ቀን ሲወሳ ያቃል ባየው አበሳ ለሱ ነው ልቤ የሚሳሳ የሮማን ግንብ ያፈረሰው ቢራራ ላፈቀረው ሰው አጃቢው ቢሆንም ሚሊዮን ሳይተካኝ በናፓሊዮን አደራ ይስጠኝ ለ ፅዮን አዛኟ እንደምትረዳኝ ከሰው ጋር ታኑረኝ አዋዳ አይፍራ ወዶ የሚፀና አይፍራ ጠብቆ ቃልኪዳን አይፍራ ለሰው የሚኖር ሰው አይፍራ ቅርብ ነው ለመዳን አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት ከፍ ከፍ ብዬ ከማጣ ፍቅር ዝቅ ዝቅ ብል አልሰኝም ቅር ሰው ወዶኝ ትልቅነቴም ይቅር በሀገር ተሞ ክብሬ ሁሉም ሰው ቢለኝ አንቱ ያለ ፍቅር ከንቱ አይደላኝ ኧረ እኔ ስሜ በመፍራቱ መውደድ ነው ኩራቱ እርቄ ከፍቅር ጎዳና አስቤ በገናገና ተብዬ ለመኖር ጀግና በፍርሃት ሰውን ለማራቅ አይደንድን ልቤ እንደ ጎልያድ እንደ ቂል ሲያሳየኝ ዘመንን ታሪኳ ሲያመጣት በዓይኔ ፍቅር ነች እራሷ ለኔ ወጣቷ ያገሬ ንግስት ሰው ነበር የልቧ ስስት ተው ጌታ ... አፍስብኝ ለዛ ተው ጌታ ... ከሰው እንዳልርቅ ተው ጌታ ... አርገኝ እንደ ዳዊት ተው ጌታ ... ቃሉ እንደሚያምርለት አፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት አጉል ክብር አግኝቼ ፍቅር ከማጣ ይበጀኛል እኔስ ከቤት ባልወጣ ወትሮም ትልቅነት መምጫው መንገዱ ሲሰጥ ነው ከላይ የሰው መውደዱ አጉል ክብር አግኝቼ ፍቅር ከማጣ ይበጀኛል እኔስ ከቤት ባልወጣ ወትሮም ትልቅነት መምጫው መንገዱ ሲሰጥ ነው ከላይ የሰው መውደዱአፍቅሬ አወድሼ እንዳገኝ ደስታ አጣፍጥልኝ ሁሌ ያፌን ጨዋታ ሁሉ እንዲሰምርልኝ በሆድኩበት የመውደድ አርግልኝ የኔን ጉልበት
Writer(s): Simone Tsegay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out