Lyrics

ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል አሀሀሀ አይኗ ሲያንፀባርቅ እንደ ኮከብ ደምቆ ሽንጧ ሲተራመስ ባ'ካሄዷ ደምቆ ከጠሩት አይኖቿ ብርሃን ይመነጫል ሽንጧ ሲተራመስ ፀጉሯም ይጫዎታል ፀጉሯም ይጫዎታል በውበት ብርሃን በመውደድ ብልጭታ ገድላ ታነሳለች በጥርሷ ፈገግታ ከንፈሯ ተላቅቆ ድምጿን ለሚሰማው ጭራሽ ሙዚቃ ነው የአእዋፎች ዜማ የአእዋፎች ዜማ ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል አሀሀሀ አንገትሽ መቃ ነው ሸምበቆ ይመስላል ለሀብሉም ለድሪው እንደልብ ይበቃል ሊታይ ፈልጎ እግሯ ሲንጠራራ ባቷን ገላመጠው ዳሌዋ እየኮራ ዳሌዋ እየኮራ ያን ሁሉ ቁንጅና ለኔ ይሁን ብሎ ዳሌዋ ይዞታል ሽንጧን ገባ ብሎ አቤቱ ነው እንጂ ለቁንጅናሽ ዳሩ ተወርቶም አይቻል ቁመናሽ ማገሩ ቁመናሽ ማገሩ አሸንክታብ ድሪ አልቦም ለእግሯ ቀርቶ ሽመል ሰውነትሽ ይታያል አብርቶ ድሪውን ጠልሰሙን ገላሽ ባያደርግም የእፍኝ እኩሌታ ውበትሽን አይነፍግም ውበትሽን አይነፍግም ለምድ እና ጎፈሬ ምን ሆነኝ ብለሽ ጌጤ መውደቂያዬ እራስ ወርቄ አንቺው ነሽ የኔ በትረ ሙሴ መጥፎሽን አልወድም ጠምበለል ነሽ ሎጋ ይህንን አልክድም ይህንን አልክድም ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል ሆድዬ የሰላም የፍቅር አንቺ ልጅ ምልክት ያሳያል ሆድዬ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out