Listen to YAHO  KENA BEL by Rophnan

YAHO KENA BEL

Rophnan

Afro-Beat

1,086 Shazams

Lyrics

በል ስማ ልቤ ስማኝ በል ቀና በል ጠና ማያልፍ የለም በተራ ጹም ፅና አይችል ድፍርስ ላይጠራ ላይቀና ሌት ላይሻል ላይበራ አትዘን ሀዘን ለማያውቅ ነፍስ ነው አውቀሀል ያወቀ ቀና መልሱ ነው ቀና ሚል አንድም ልቡ ደነደነ ቀና ባይ አንድም ጌታን አመሰገነ ያ ቀና ባይ ክዶህ ጣለህ አድጦ ሲቀር ያ ቀና አባይ ደርሶ ወለደ አምጦ ፍቅር ያ ሰው አዳኝ አስራ ሁለት አርጎ ሲመርጣቸው በቃል ሰው አዳኝ አርጎ ለአለም አተረፋቸዉ ሰው መራጩን እርሳስም ቀራጩን ሳለ እንጨት ፈላጩን አሳውም አጥማጁን ሳበ ሌባ ፈራጁን አያ በሬም ከአራጁ ዋለ ሰውም ከራሱ ካልታረቀ እራሱን ጣለ ፍቅር ይወዳል እውነት እውነትም ይወልዳል ብዙ የብዙም ሀይሉ ክብድ ነው ከባድስ ማነው እንደርሱ እርሱን የታመነች ፀሀይ አትችልም ማልዳ ልትቀር ላንተም አለህ ቀን ቀና በል በለው ብርርርርር አለች ልቤ ካፌ ደርሳ ያኔ ክርርርርር አለች ማህተቤ አንገት ይዛ አየው ብርርርርር ማይገዛው ነገር እልፍ ነው እውነት ብርርርርር ሰው ገበያት ባመነው አንቺ እታለም ይሄም ያልፋል ግድየለም ቀና ወንድም አለም አንተም ቀና እንደ እታለም በላ አይዞን አንቺ እታለም ይሄም ያልፋል ግድ የለም ቀና ወንድም አለም አንተም ቀና እንደ እታለም በላ አይዞን (አይዞን) ጠብታ ሚስጥር ውስጧ ደብቃ ኖራ ታምቃ ከደመናው ታዝላ ቆይታ ዘነበች ምድርን አጠበች ማሳ አረጠበች መሬት ገብታ እህል አበቀለች አለምን መገበች ጠብታን ማይንቅ ገበሬ ዘርቶ ያፈራው ተበላ አሽቶ እያፈራ ጥሬ እና ፍሬ በሰኔ ጠብ ይላል ብሎ አማኝ ገበሬ ለሰማይ ፀሎት ሊነግር ቀና አለ ዛሬ ሮፍናን አመነ እንዳለ ነገ ሌላ እንደሆነ ቃኘ መዘነ መተረ ሰው ብሎ ዳኘ ሰመረ አሸንፎ ታየ ማጣት እንዳለ ማግኘትን ቃኘ መኖር እንዳለ መሞትን አየ ይመሻል ይነጋል ይጠፋል ይመጣል በነገሮች ሁሉ ቀና ብሎ አየ አንቺ እታለም ይሄም ያልፋል ግድ የለም ቀና ወንድም አለም አንተም ቀና እንደ እታለም በላ አይዞን (አይዞን) አንቺ እታለም ይሄም ያልፋል ግድ የለም ቀና ወንድም አለም አንተም ቀና እንደ እታለም በላ አይዞን (አይዞን) ያሆ ያሆ ያሆ ያሆ አንቺ እታለም ይሄም ያልፋል ግድ የለም ወንድም አለም አንተም ቀና እንደ እታለም ያሆ ያሆ ያሆ ያሆ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out