Lyrics

ቃሉ ሲያስተምረን ፣ መንፈሱ ሲያፅናናን አቻምናን አለፍን ተሻገርን አምናን ጠላት ቢቃወመን ፣ እጅግ ተገዳድሮ ጌታ ተዋግቶልን ደረስን ዘንድሮ ፣ ደረስን ዘንድሮ ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ መጻተኞች ብንሆን ፣ ምድር ያልተገባን ምንም አልጎደለን ለኛ ከሚረባን ወላጅ እንደሌለው ፣ ልጅ አላደረገን የሁላችን አባት እግዚአብሔር ይመስገን ፣ እግዚአብሔር ይመስገን ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ ጉንድሹ ቢመጣ፣ አካሉ ተሟልቶ አውሩ በወጣ ሄደ አይኑ ተከፍቶ ሙታን ተነስተዋል ፣ የተራቡም በሉ እጁን ከዘረጋ ይደርሳል ለሁሉ ፣ ይደርሳል ለሁሉ ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንልህ ህዝቡ እንደሆነ አይቀር ፣ ተስፋውን መውረሱ ፈርኦን ለምን ነው ሃይሉን መጨረሱ ባህር ተከፈለ ፣ በድል ተሻገሩ እንዴ እስከ ዘላለም ተሰብሯል ቀንበሩ ፣ ተሰብሯል ቀንበሩ ተራራ የሚናድለት ፣ ጨለማ ሚገፈፍለት ነፋሳት የሚገዙለት ፣ ወጀቡ ሚታዘዝለት እየሱስ እየሱስ ክብር ይሁንለት
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out