Top Songs By Jordan & Bek Ge'ez
Lyrics
ጆርዳን ኤንድ ቤክ ግዕዝ
ከማይመች ዓለም
ከማይመች ሰዉ አመል
ነፍሴን ጣር ይዟታል
የግድ ኑሮ ከብዷታል
ግን ለምን ከፋ የሰዉ ደጅ
ያኔ ማያዉቀዉ አማላጅ
እንደዉ ላይሞላ
የሚያስጨንቀኝ
የሒወት ባዶነት አሁን ገባኝ
ሳዝን ሰንብቼ
ደግ ቀን ይመጣል እያልኩ ክፋዉን ቀን አልፌ
አይኔ ደም ለብሶ
ትላንትን ባየበት በዛሬ አልቅሶ
አመት አልሜዉ
ላልችለዉ ነገር
ዛሬን ልርሳዉ በቃ
መጨነቄም ይቅር
የቃየል ጊዜ ዛሬ አበቃ
የላዩን ይዤ ልኑር በቃ
በእኔ አልቀረም
መሽቶ ቀኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
አንደዉ ላይሞላ
የሚያስጨንቀኝ
መሽቶ እንደሚነጋ አሁን ገባኝ
የቃየል ጊዜ ዛሬ አበቃ
የላዮን ይዤ ልኑር በቃ
በእኔ አልቀረም
መሽቶ ቀኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
ይኸዉ ታየኝ ወጋገኑ
ወጋገኑ
Lyrics powered by www.musixmatch.com