Lyrics

የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ ውበት የታደለች የቀይ ዳማ ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ ውበት የታደለች የቀይ ዳማ ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ የገላዋ ድምቀት እልፍኝ ያካልላል የአይን አሰናዘሯ ጎበዝ ያባንናል ማዕዛ ጠረኗ ጭምት ያዋልላል ወድጃት ብረታ ማን ሰምቶ ጉድ ይላል አካል ሰውነቴን እንዳለ ዋተተ ተስካር አውጪ እንግዲ ልቤ ለሰው ሞተ ብሞት ቁም አትብሉ ቢፈርስ አካላቴ እርም የለኝ በፍቅር አይቆርጥም አንጀቴ መነኩሴ ሲያግባባ ቃልሽ አንደበት ደምግባት ውበትሽ ቢሆን ማን ፈረደ ገላዬ ግዛትሽ ቅርሴ ሰውነትሽ የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ ውበት የታደለች የቀይ ዳማ ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ ናፍቆት ጭጋግ ጥሎ በኔው ከደመነ ደቦ እንተጋገዝ ልብሽ ሰው ካመነ ትካዜን አበዛ ልቤን ደስታ ርቆት ባጥቢያ ኮከብ ድረሽ አስጨነቀኝ ናፍቆት የካበችውን ቃል ምን ይሆን ማፍረሷ የጎጆዬ ባላ የወደቀው በእሷ ከራቀች አትመጣ ማዘን አታውቅበት እስቲ ገል አጋዙኝ ቤቴን ላሙቅበት ምለሽ አልነበር ወይ የልቤን ወዳጅ በግቢም በደጅ ብታውቂም ከተማ መንገድ ብትለምጂ ሄደሽ አትቅሪ እንጂ የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ ውበት የታደለች የቀይ ዳማ ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ ውበት የታደለች የቀይ ዳማ ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ የዘመንን ለቅሶ ትቼው በጅምር እሷ በዘገየች እዋተት ጀመር ችግር አይታክቴ ልቤ ገራገሩ ናፍቆት ይዞት ሄደ ወጣ ከመንደሩ ውጪ በልደታው አንቺ ልጅ ከቤትሽ ይሳሉብሽ እንደው በደማምነትሽ አካልሽ በማሾ ሊሰየም ምን ቀረው እስኪ ለሰው ታይ ብርሀን ለቸገረው ተነስተሽ ውጪና ቁሚ ከደጃፉ እያዩሽ ይለፉ ተንጎራደጂና ይታይልኝ ጉዴ ቆንጆ የመውደዴ ቆንጆ የመውደዴ ቆንጆ የመውደዴ ቆንጆ የመውደዴ ቆንጆ የመውደዴ
Writer(s): Ephrem Tamiru Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out