Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Ephrem Tamiru
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Ephrem Tamiru
Songwriter
Lyrics
የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ
ውበት የታደለች የቀይ ዳማ
ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ
ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ
የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ
ውበት የታደለች የቀይ ዳማ
ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ
ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ
የገላዋ ድምቀት እልፍኝ ያካልላል
የአይን አሰናዘሯ ጎበዝ ያባንናል
ማዕዛ ጠረኗ ጭምት ያዋልላል
ወድጃት ብረታ ማን ሰምቶ ጉድ ይላል
አካል ሰውነቴን እንዳለ ዋተተ
ተስካር አውጪ እንግዲ ልቤ ለሰው ሞተ
ብሞት ቁም አትብሉ ቢፈርስ አካላቴ
እርም የለኝ በፍቅር አይቆርጥም አንጀቴ
መነኩሴ ሲያግባባ ቃልሽ አንደበት
ደምግባት ውበትሽ
ቢሆን ማን ፈረደ ገላዬ ግዛትሽ
ቅርሴ ሰውነትሽ
የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ
ውበት የታደለች የቀይ ዳማ
ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ
ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ
ናፍቆት ጭጋግ ጥሎ በኔው ከደመነ
ደቦ እንተጋገዝ ልብሽ ሰው ካመነ
ትካዜን አበዛ ልቤን ደስታ ርቆት
ባጥቢያ ኮከብ ድረሽ አስጨነቀኝ ናፍቆት
የካበችውን ቃል ምን ይሆን ማፍረሷ
የጎጆዬ ባላ የወደቀው በእሷ
ከራቀች አትመጣ ማዘን አታውቅበት
እስቲ ገል አጋዙኝ ቤቴን ላሙቅበት
ምለሽ አልነበር ወይ የልቤን ወዳጅ
በግቢም በደጅ
ብታውቂም ከተማ መንገድ ብትለምጂ
ሄደሽ አትቅሪ እንጂ
የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ
ውበት የታደለች የቀይ ዳማ
ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ
ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ
የድንገት እንግዳ ውብ አይናማ
ውበት የታደለች የቀይ ዳማ
ተናፋቂ ጠረን ተሸልማ
ልቤን ነስታኝ ሄደች በእኔ አድማ
የዘመንን ለቅሶ ትቼው በጅምር
እሷ በዘገየች እዋተት ጀመር
ችግር አይታክቴ ልቤ ገራገሩ
ናፍቆት ይዞት ሄደ ወጣ ከመንደሩ
ውጪ በልደታው አንቺ ልጅ ከቤትሽ
ይሳሉብሽ እንደው በደማምነትሽ
አካልሽ በማሾ ሊሰየም ምን ቀረው
እስኪ ለሰው ታይ ብርሀን ለቸገረው
ተነስተሽ ውጪና ቁሚ ከደጃፉ
እያዩሽ ይለፉ
ተንጎራደጂና ይታይልኝ ጉዴ
ቆንጆ የመውደዴ
ቆንጆ የመውደዴ
ቆንጆ የመውደዴ
ቆንጆ የመውደዴ
ቆንጆ የመውደዴ
Writer(s): Ephrem Tamiru
Lyrics powered by www.musixmatch.com