Lyrics

እድሜ መገስገሱን ከቶ ሰው ዘንግቶት ነገ አልፎልኝ ይላል ማለፉን ረስቶት አሄ ማለፉን ረስቶት አይቀር መንፈራገጥ የሆድ እስኪሞላ ወድቃ እስክትሰበር ህይወት እንደ ሸክላ አሄ ህይወት እንደ ሸክላ ጣሪያና ግድግዳው በወርቅ ቢሰራ ገንዘብ ተቆልሎ ቢመስል ተራራ አሀ ቢመስል ተራራ በከፋው ጨለማ በዛ በሞት መንገድ ተከትለው አይሄድም ሀብት የስጋ ዘመድ አሀ ሀብት የስጋ ዘመድ ያለዉ ከሌለው ጋር ተካፍሎ እንደመብላት ለምን ይስታል እድሜ አይለውጥም ሀብት የሌለው ዘመዱን ሸኝቶት በጥርሱ ችግር ይዘው ሲሞት ምንድነው ማልቀሱ
Writer(s): Elias Woldemariam, Abrishe Zeget Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out