Lyrics

እንደ ገብሱ ዛላ የኔ ዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ መላው ሰውነቷ የኔ ዓለም በመውደድ ተክኖ አይነ ኮኮብ ጉብል የኔ ዓለም የደስደስ የዋጣት አስታውላኝ ሄደች የኔ ዓለም የተዋበች ወጣት የዘንድሮ ክረምት አጉረመረመና ሐምሌና ነሐሴ አጥግቦታልና አሳየኝ ይሄ ዓመት አሄ ያቺን መልከ ቀና እንዲህም አልነበር ያቻምና ሃሳቤ እንዲህም አልነበር ያቻምና ሃሳቤ እንደው በቆንጆ ልጅ አሄ ተጨነቀ ልቤ ዉበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ ዉበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ አሸነፈኝ ቃሏ አሄ ብታነጋግረኝ እንደ ገብሱ ዛላ የኔ ዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ መላው ሰውነቷ የኔ ዓለም በመውደድ ተክኖ አይነኮኮብ ጉብል የኔ ዓለም የደስደስ የዋጣት አስታውላኝ ሄደች የኔ ዓለም የተዋበች ወጣት ሸጋ የለም ብዬ አውነት ነው ተብሎ ቆንጆ የለም ብዬ እውነት ነው ተብሎ ጉድ አረገኝ አባይ አሄ ጠምበለል አብቅሎ ሐምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራቱ ሐምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራቱ በጋውም ደረሰ አሄ ተሸኘ ክረምቱ ያችስ የፍቅር ሰው ምነው ታዲያ አትመጣም ያችስ የፍቅር ሰው ምነው ታዲያ አትመጣም እያየ ልበል አሄ ልቤ እየተቀጣም እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ መላው ሰውነቷ የኔዓለም በመውደድ ተክኖ አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም የደስደስ የዋጣት አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብዬ ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብዬ ቤቱ ባደስ ደምቆ አሄ ፍርዳየን ጥዬ ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ ደሞ ከዳኝ ልቤ አሄ ወደ አንቺው ተሸኘ አይግጠም ነው እንጅ መቼም ከገጠመ ልብ እንደ ሁዳዴ እየቆረጠመ የዞረ ያስፈታል አሄ የተጠመጠመ እንደ ገብሱ ዛላ የኔዓለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ መላው ሰውነቷ የኔዓለም በመውደድ ተክኖ አይነኮኮብ ጉብል የኔዓለም የደስደስ የዋጣት አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት አስታውላኝ ሄደች የኔዓለም የተዋበች ወጣት
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out