Lyrics

ና ና ዘመዴ አረ ያገሬ ልጅ አረ ያገሬ ልጅ ና ዘመዴ አለው አለውና ሲዘፈን በጎንደር ንቅሳት ጌጥ እንጂ መች መለያ ነበር ልረሳህ እልና ልተወው እልና ያገረሽብኛል ፍቅርህ እንደገና ና ምነው ና ምነው ና ምነው ፍቅር ካገር ልጅ ነው ተው ምነው ተው ምነው ተው ምነው ልቤ ባንተ ላይ ነው እንዲያው ዞማ ዞማ ሆዴ ዞማ ዞማ ወይ በቀን አትመጣ አትከሰት ባካል ሌት የማያስተኛው ትዝታህ ይተካል ደከመኝ አንተዬ ታከተኝ አንተዬ ናፍቆት መውደድ ህመም ስንቱን አባብዬ ሆዴ ዞማ ዞማ ፍቅር ዞማ ዞማ ማነው ወደ እሱ ቤት ስቦ የሚወስደኝ ለምንድን ነው ከቶ እሱን ያስወደደኝ አረ ጎኔ አልቻለም አረ ሆዴ አልቻለም እንኩዋን እኔን እና ሰነፍ ደካማይቱን ፍቅር በጀግኖች ላይ ገልጧል ጀግንነቱን አረ ሆዴ አልቻለም አረ ጎኔ አልቻለም ና ና ዘመዴ አረ ያገሬ ልጅ አረ ያገሬ ልጅ ና ዘመዴ አለው አለውና ሲዘፈን በጎንደር ንቅሳት ጌጥ እንጂ መች መለያ ነበር ልረሳህ እልና ልተወው እልና አገርሽቶ ያድራል ፍቅርህ እንደገና ና ምነው ና ምነው ና ምነው ፍቅር ካገር ልጅ ነው ዞማ እንዲያው ዞማ ዞማ ዞማ ሆዴ ዞማ ዞማ መች በላሁና መቼ ጠጣሁና መች ጤና ዋልኩና መች ጤና አደርኩና ከማይታለፈው ፅፎኝ ከፈተና ዞማ ሆዴ ዞማ ዞማ ዞማ አንተ ዞማ ዞማ እንኳን በርትቼ አይቶኝ እንኳንስ ቆሜና ወድቄም አይለቀኝ ያንተ ፍቅር ገና ተወኝ ተወኝ ተወኝ ብተወኝ ምናለ ከገደሉ ወዲያ ሌላም መግደል አለ ሆዴ ዞማ ዞማ ዞማ ፍቅር ዞማ ዞማ ዞማ አለም ሆዴ አልቻለም አረ ጎኔ አልቻለም ማነው ወደ እሱ ቤት ስቦ የሚወስደኝ ለምንድን ነው ከቶ እሱን ያስወደደኝ አረ ጎኔ አልቻለም አረ ሆዴ አልቻለም ለማን የው አሽከላው ለማና ነው ወጥመዱ የወደቀ አታውቅም በገዛ ፍቃዱ
Writer(s): Elias Woldemariam, Abebe Birhane Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out