Lyrics

ጉድ ያረገኝ ዓይኔ ነው ኣይቶሽ በክፉ ቀን እንድግባባሽ ፈልጌ ሰው ቢያስተዋውቀን ኣሳፍረሽኝ መውደዴን ልነግርሽ ብሞክር ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር እንኳን ተናግረሽኝ በሰው ፊት ዓይንኣፋር ነኝ እኔ ከበፊት ደፍሬ ባወራሽ አንቺን ብቻ አደረግሽኝ የሰው መዛበቻ ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ ልክ እንደ ህጻን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ ስፈራ ስቸር አናግሬሽ ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ ስፈራ ስቸር አናግሬሽ ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ) ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ) ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ ድሮም ዓይንአፋር ነኝ (እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ) ድሮም ዓይንአፋር ነኝ ጉድ ያረገኝ ዓይኔ ነው (ኣሃሃ) ኣይቶሽ በክፉ ቀን እንድግባባሽ ፈልጌ ሰው ቢያስተዋውቀን ኣሳፍረሽኝ መውደዴን ልነግርሽ ብሞክር ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ የማይገባሽ ፍቅር ሰው ቢያደፋፍረኝ እንድነግርሽ ብዬ አሸንፎኛል በቃ ፍቅርሽ ገና ሳይሽ ጠፋኝ ምገባበት ፊት ነሳሽኝ እና ሰው ባለበት ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ ልክ እንደ ህጻን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ ስፈራ ስቸር አናግሬሽ ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ ፍቅሬን መግለጼ ም ክፋት አለው ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ ስፈራ ስቸር አናግሬሽ ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ) ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ ተይ እዳ ኣሃሃ እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ ድሮም ዓይንአፋር ነኝ
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out