Lyrics

በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ ባስበው ተጉዤ ወደኋላ እኔስ አጣሁ መላ ይቅርና ማሰብ በትካዜ አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ በሃሳብ አስታውሼ ወደኋላ እንባ ባይኔ ሞላ ይቅርና ማሰብ በትካዜ አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ ክፉ ደግ ላሳየኝ በህይወት ዘመኔ ክብሩ ይመስገን ለአምላክ ልበል አስቀድሜ በአራቱም ቅኝቶች ዜማን ተቀኝቼ ቅርስ አስረክቤአለሁ ላሉት ወገኖቼ አንቺ ሆዬ ባቲ አምባሰል ትዝታ ከነፍስህ የወጣው የጥበብ ስጦታ ያወረስከን ሙያ ሳይቀር ተደብቆ ይኖራል ከኛ ጋር ክብርህን ጠብቆ አደራ እላለሁ ደግሜ ለጥበብ በቆየው ስሜ አትዘን ሃሳብ አይግባህ ያፈራል ዛሬም አበባህ አይባባም አይባባም ሆዴ አይባባም አይባባም ሆዴ እስካለ መጪው ትውልዴ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ሙያዬን የሚቀበለኝ በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ ባስበው ተጉዤ ወደኋላ እኔስ አጣሁ መላ ይቅርና ማሰብ በትካዜ አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ በድንገት ያለፈውን ጊዜ በትዝታ በሃሳብ አስታውሼ ወደኋላ እንባ ባይኔ ሞላ ይቅርና ማሰብ በትካዜ አጫውተኝ ስላለፈው ጊዜ የዘመኔን ዋርካ ግንዱን ተጠግቼ ይኸው አዜማለሁ ዕውቀቱን አግኝቼ ከቀደሙኝ ማወቅ ሆኖልኝ መላዬ ተምሬአለሁ ብዙ እኔም ከ ጥላዬ ያሬዳዊ ዜማ በሚያንቆረቁረው ተቀበልኩ አደራ በድምፅህ በሚያምረው መቼም ላላጠፋው ጥበብን ከደሜ ባገር ፊት ቃል ልግባ ከመድረኩ ቆሜ አደራ እላለሁ ደግሜ ለጥበብ በቆየው ስሜ አትዘን ሃሳብ አይግባህ ያፈራል ዛሬም አበባህ አይባባም አይባባም ሆዴ አይባባም አይባባም ሆዴ እስካለ መጪው ትውልዴ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ሙያዬን የሚቀበለኝ አይባባም አይባባም ሆዴ እስካለ መጪው ትውልዴ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ሙያዬን የሚቀበለኝ አይባባም አይባባም ሆዴ አይባባም አይባባም ሆዴ እስካለ መጪው ትውልዴ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ዛሬማ ተተኪም አለኝ ሙያዬን የሚቀበለኝ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out