Lyrics

እስከዛሬ ፡ የጠበቀኝ ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ያለቀቀኝ የክርስትናን ፡ ቀጭን ፡ መንገድ ፡ የሕይወትን ፡ ውጣ ፡ ውረድ ባይበዛልኝ ፡ የእርሱ ፡ ፀጋ ፡ አንዷም ፡ ሌሊት ፡ አትነጋ ዛሬም ፡ ቆምኩኝ ፡ በዚህ ፡ ቦታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ባይበዛልኝ ፡ የእርሱ ፡ ፀጋ ፡ አንዷም ፡ ሌሊት ፡ አትነጋ ዛሬም ፡ ቆምኩኝ ፡ በዚህ ፡ ቦታ ፡ ስሙ ፡ ይክበር ፡ የእኔ ፡ ጌታ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና እንደጠላት ፡ አሳብ ፡ ቢሆን ፡ ከሆነልኝ ፡ አንዱም ፡ አይሆን ታሪክ ፡ ቢያብብ ፡ ሕይወት ፡ ቢያምር ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ በእርሱ ፡ ተዐምር ከእያንዳንዷ ፡ እስትንፋስ ፡ ስጦታ ፡ ናት ፡ የኢየሱስ ከፈቀደ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ የሚል ፡ ማን ፡ አለ ከእያንዳንዷ ፡ እስትንፋስ ፡ ስጦታ ፡ ናት ፡ የኢየሱስ ከፈቀደ ፡ ይሁን ፡ ካለ ፡ አይሆንም ፡ የሚል ፡ ማን ፡ አለ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና አንተ ፡ . ጥላቴ ፡ ቀናተኛ ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አትተኛ እንደተራበ ፡ አንበሳ ፡ ዙሪያዬን ፡ ብትዞር ፡ እያገሳህ ልትውጠኝ ፡ ብትመኘኝ ፡ ሲያምርህ ፡ ይቅር ፡ አታገኘኝ በስሙ ፡ አጥር ፡ በደሙ ፡ እሳት ፡ ከልሎኛል ፡ የእኔ ፡ አባት ልትውጠኝ ፡ ብትመኘኝ ፡ ሲያምርህ ፡ ይቅር ፡ አታገኘኝ በስሙ ፡ አጥር ፡ በደሙ ፡ እሳት ፡ ከልሎኛል ፡ የእኔ ፡ አባት ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያልቅምና ያንን ፡ ዘንዶ ፡ እባቡን ፡ የወጋኸው ፡ ወገቡን ራስ ፡ እራሱን ፡ ያስረገጥከኝ ፡ ስንቱን ፡ ነገር ፡ ያስመለጥከኝ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጋሻዬ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ መቆሚያዬ ፡ ነህ ፡ አለቴ ፡ ላመስግንህ ፡ በአንደበቴ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጋሻዬ ፡ በክፉ ፡ ቀን ፡ መሸሺያዬ መቆሚያዬ ፡ ነህ ፡ አለቴ ፡ ላመስግንህ ፡ በአንደበቴ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ አላለቀምና ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ምህረትህ ፡ ቸርነትህ ፡ ከቶ ፡ አያbልቅምና
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out