Lyrics

ምን ምን ውዬልሽ ይሆን ምን አድርጌልሽ ስታሞጋግሺኝ ውለሽ ማደርሽ ያንቺስ መልካምነት መች ያልቃል ተቆጥሮ መፅሐፍ ይወጣዋል ቢፃፍ ተዘርዝሮ እንዲያው ምን ምን ውዬልሽ ይሆን ምን አድርጌልሽ ስታሞጋግሺኝ ውለሽ ማደርሽ ያንቺስ መልካምነት መች ያልቃል ተቆጥሮ መፅሐፍ ይወጣዋል ቢፃፍ ተዘርዝሮ እሩቅ ጥልቁ ፍቅርሽ ፅናት ትዕግሥትሽ ቅንነት ደግነት ታማኝነትሽ እንደሷ አይነት ፍጡር አለች ወይ እስኪባል ስላንቺ ሲነገር ሰው ሁሉ ጉድ ይላል ጤና ይስጥሽ እንጂ እድሜሽን አርዝሞ እኔ ያንቺን ውለታ አልከፍልም ፈፅሞ ጤና ይስጥሽ እንጂ እድሜሽን አርዝሞ እንቅፋት አይንካሽ አንቺንስ ፈፅሞ ሰላም ሁኚልኝ ሁኚልኝ ደህና ሁኚልኝ ሁኚልኝ ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ አትከፊብኝ ሰላም ሁኚልኝ ሁኚልኝ ደህና ሁኚልኝ ሁኚልኝ ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ ሳትከፊብኝ ምን ምን ውዬልሽ ይሆን ምን አድርጌልሽ ስታሞጋግሺኝ ውለሽ ማደርሽ ያንቺስ መልካምነት መች ያልቃል ተቆጥሮ መፅሐፍ ይወጣዋል ቢፃፍ ተዘርዝሮ ትሁትነትሽን ለማንም አልሰጠው ሊያስተምርብሽ ነው አንቺን የመረጠው አሁን ባለንበት በሚታማው ዘመን ያንቺ አይነቱን ያብዛው ብሎ ነው መለመን ጤና ይስጥሽ እንጂ እድሜሽን አርዝሞ እኔ ያንቺን ውለታ አልከፍልም ፈፅሞ ጤና ይስጥሽ እንጂ እድሜሽን አርዝሞ እንቅፋት አይንካሽ አንቺንስ ፈፅሞ ሰላም ሁኚልኝ ሁኚልኝ ደህና ሁኚልኝ ሁኚልኝ ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ አትከፊብኝ ሰላም ሁኚልኝ ሁኚልኝ ደህና ሁኚልኝ ሁኚልኝ ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ አትከፊብኝ ሰላም ሁኚልኝ ሁኚልኝ ደህና ሁኚልኝ ሁኚልኝ ሁሌም በደስታ ኑሪልኝ ሳትከፊብኝ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out