Lyrics

የምለምንህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ አትሂድ የምልህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ አንተን ካጣው መኖር የማልችል ነብሴ በእጅህ ያለች ይመስል ምነው ይሄን ያህል ምነው ይሄን ያህል ምነው ይሄን ያህል እንዴ ምነው ይሄን ያህል ልቤ እንደሚያፈቅርህ አውቃለው አልክድም ባንተላይ ጨክኖ አንጀቴ ባይቆርጥም አይገለኝም ብትሄድ ፍቅር እንደ ውሀ ጥም ካንተ መለየቱ ምን ሆዴን ቢያስብሰው እህል አልጣ እንጂ ምበላው ምቀምሰው ፍቅርን ተርቦ የለም የሞተ ሰው በቃ ልሂድ ካልክ በቃ ሂድ በቃ ታዲያ እስከመቼ ነፍሴ ተጨንቃ አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና አንተን አጥቼ አልሞትም እና አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ ከበቃህ ይብቃ የምለምንህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ አትሂድ የምልህ ወድጄህ ወድጄህ አፍቅሬህ እንጂ አንተን ካጣው መኖር የማልችል ነብሴ በእጅህ ያለች ይመስል ምነው ይሄን ያህል ምነው ይሄን ያህል ምነው ይሄን ያህል እንዴ ምነው ይሄን ያህል እንደ ውጥናችን ያኔ እንደጀመርነው ተፈላልገን እንጂ ቢሆን ደስ የሚለው ፍቅር በልመና የማይሆን ነገር ነው አልዘልቀውምና ሁሌም ተማፅኜ ለኔ እዳልተፈጠርክ ውስጤን አሳምኜ ያላንተ መኖርን ልየው ደሞ ወስኜ በቃ ልሂድ ካልክ በቃ ሂድ በቃ ታዲያ እስከመቼ ነፍሴ ተጨንቃ አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና አንተን አጥቼ አልሞትም እና አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ ከበቃህ ይብቃ አይንሳኝ እንጂ እድሜና ጤና አንተን አጥቼ አልሞትም እና አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ አታስፈራራኝ ከበቃህ ይብቃ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out