Lyrics

የዚች አለም ዝና ያልፋል እንደ ጥላ ሀብትና ንብረትም ይቀራል ከኌላ ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ እንደባህር አሸዋ ልክ እንደዋክብት በዕድሜሽ ቁጥር ላይ ቁጥር ይለቅበት መቆምሽ ነውና እኔን የሚያቆመኝ ባንቺ ቦታ ልዋል ህመምሽ ይመመኝ ባንቺ ቦታ ልዋል ህመምሽ ይመመኝ ኑሪልኝ ኑሪ ኑሪልኝ አንቺን ያቆይልኝ ኦ ፣ ኦሆ ፣ ዎሆ ፣ ሆሆ ፣ አሀ ሀሀ ፣ ሀሀ የዚች አለም ዝና ያልፋል እንደ ጥላ ሀብትና ንብረትም ይቀራል ከኌላ ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ ሳይኖራት አመስጋኝ ፀዳል ብርሀኔ እናት አበባዬ ትኑርልኝ ለኔ ጊዜ ተገዝቶልሽ ታዞልሽ ዘመኑ የዕድሜሽ ዳርቻ ጥልቅ ይሁን ወሰኑ ነፃ እንዳወጣሽ አዝለሽ የኔን ቀንበር ላንቺ ብቻ ሲባል ሞት ባይኖር ምን ነበር ላንቺ ብቻ ሲባል ሞት ባይኖር ምን ነበር ኑሪልኝ ኑሪ ኑሪልኝ አንቺን ያቆይልኝ ኦ ፣ ኦሆ ፣ ዎሆ ፣ ሆሆ ኑሪልኝ ቆዪልኝ ቆዪልኝ እናቴ ቆዪልኝ ቆዪልኝ ቆዪልኝ አንቺን ያኑርልኝ አንቺን ያኑርልኝ አንቺን ያኑርልኝ ኑሪልኝ ቆዪልኝ ቆዪልኝ አንቺን ያኑርልኝ ሆሆ አሀሀ ሀሀ ሆሆ ሆሆ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out