Lyrics

እምቢ እንዳልኩህ አላውቅም በጭራሽ ያስተዋልኩት ሰው ሲለኝ ነው ኮራሽ ለኔ ባይልህ ስትውል ባይኔ መች ቀረልኝ መብከንከኔ ስትቀርበኝ ሸሽቼህ አፍሬ ስትርቀኝ ልመጣ አፍቅሬ መች ገባኝ ዞሬ እንደምመለስ ማለዳ ማለዳ ማለዳ ነው አሉ መውደድና ፍቅር ልብ የሚባባሉ ማለዳ ማለዳ ማለዳ መጥቼ ልመለስ ብቆጭም ዐይንህን አይቼ ለማን ለማን ለማን ለማን ሊልህ ነው ለማን ሊልህ ነው ፍቅር አንተን ሲተው እኔን ያለኝ አልተው ወይ አኩራርቶኝ መፈቀሬ ልዋልልህ ተግደርድሬ አንዴ ከእጄ አምልጠሃል ሸጋ መውደድ ወጥነሃል ኧረ አንዳንዴ ኧረ አንዳንዴ ሰው በመላ ነው በዘዴ የሚያዘው ሲሉኝ ያኔ መች ታወቀኝ ይሄ ለኔ ገባኝ ብል ነገሩ ካለፈ ፍቅርህ ግን ለኔ መች ተረፈ ነገዬን ሳስብ ከበፊቱ ገደለኝ ፀፀቱ ቁጭቱ ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም ማለዳ ማለዳ ማለዳ ነው አሉ መውደድና ፍቅር ልብ የሚባባሉ ማለዳ ማለዳ ማለዳ መጥቼ ልመለስ ብቆጭም አይንህን አይቼ በማን በማን በማን በማን ሊክሰኝ በማን ሊክሰኝ ይሆን ሆድ ያስባሰኝ አንሶ የሚያስነክሰኝ ይብላኝ እንጂ ለኔው ገላ አሻፈረኝ ላለኝ ሌላ ይሁን ብልስ እሺ በቃ የት ይገኛል የልብ አውቃ ጥሩ አንዳንዴ ጥሩ አንዳንዴ ሰው በመላ ሰው በዘዴ ባላልኩበት ዘመን ያኔ ነበር ለካስ ልብህ የኔ ገባኝ ብል ነገሩ ካለፈ ፍቅርህ ግን ለኔ መች ተረፈ ነገዬን ሳስብ ከበፊቱ ገደለኝ ፀፀቱ ቁጭቱ ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም ቆጨኝ በጣም ቆጨኝ በጣም በጣም ቆጨኝ በጣም ስትለኝ አልመጣም ቆጨኝ በቃ ቆጨኝ በቃ በጣም ቆጨኝ በጣም የዕድሌን ባላጣም
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out