Lyrics

እኔ ጥቁሬ ብስሬ ሆይ አንድ አንኳር ጨዋታ ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ ዙሪያው በራ ስትስቂ ለውበትሽ ምን ይደገስ ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ ዙሪያው በራ ስትስቂ ለውበትሽ ምን ይደገስ ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ ልብሽ እና ቀልብሽ ከሰማይ ሲርቅ ምን ሆኜ ልገለጥ ባይንሽ እንድደምቅ ላገኛት ነው እያልኩ ዋልኩኝ በሰመመን አግኝቼ እስከማቅፍሽ የቀን ህልሜን ልመን (እና) ባይንሽ ላልሞላ (እና) በጌጥ በልብሴ (እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ (እና) ተጋረደብኝ (እና) መላና ዘዴ (እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ በአንድ እጇ አምባር አላት በአንድ እጇ የላትም እንደንጉሥ ሀገር ሰው አይለያትም ወንዙ ሞልቶ ቢፈስ እሷ ምን ቸገራት (እና) ወዳጇ ብዙ ነው ወድቆ ሚያሻግራት ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ ዙሪያው በራ ስትስቂ ለውበትሽ ምን ይደገስ ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ ዙሪያው በራ ስትስቂ ለውበትሽ ምን ይደገስ ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ ባ'ገር በመንደሬ ሚታገለኝ የለም ማንን ልርታ ይሆን በ'ጅሽ እንድሸለም የኑሮዬን ጣጣ በፍቅርሽ ረሳሁ አስቤሽ ተኝቼ ደስ ብሎኝ ተነሳሁ (እና) ባይንሽ ላልሞላ (እና) በጌጥ በልብሴ (እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ (እና) ተጋረደብኝ (እና) መላና ዘዴ (እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ በአንድ እጇ አምባር አላት በአንድ እጇ የላትም እንደ ንጉሥ ሀገር ሰው አይለያትም ወንዙ ሞልቶ ቢፈስ እሷ ምን ቸገራት (እና) ወዳጇ ብዙ ነው ወድቆ ሚያሻግራት አለ አንኳር ጨዋታ አለ አንኳር ጨዋታ ሲካሱ በመውደድ የማታ የማታ አለ አንኳር ጨዋታ አለ አንኳር ጨዋታ ሲካሱ በመውደድ የማታ የማታ (እና) ባይንሽ ላልሞላ (እና) በጌጥ በልብሴ (እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ (እና) ተጋረደብኝ (እና) መላና ዘዴ (እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ እና
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out