Lyrics

ያልፋል ይህ ሃሳብ ያልፋል ይህ ደመና ከፋም ያሉት ቀን ከፍ ያደርጋል ገና ያልፋል ይህ ንፋስ ያልፋል ይህ ደመና መልካም ይሆናል መልካም ነበርና ያልቃል ሲሉት እየሰፋ ቀን ሲመስል ማይገፋ መንገድ አለ መውጫ ቦታ ቀን ይመጣል በቀን ፋንታ ይለካዋል ወርቅ ብርታቱን ማለፊያ ነው ብሎ እሳቱን ተስፋ ከእምነት ከተሰራ ያሻግራል ከመከራ ማለፊያ ሲል ነው ማለፊያ ሰው የማይድን ከሃሳብ ጥድፊያ ማለፊያ ሲል ነው ማለፊያ ሰው የማይድን ከሃሳብ ካፊያ ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ችግር ፈተናው (ያልፍል እንደ ጉም) ቢልም ጉም ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ችግር ፈተናው (ያልፍል እንደ ጉም) ቢልም ጉም ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፋል ይህ ሃሳብ ያልፋል ይህ ደመና ከፋም ያሉት ቀን ከፍ ያደርጋል ገና ያልፋል ይህ ንፋስ ያልፋል ይህ ደመና መልካም ይሆናል መልካም ነበርና ያጡትን ለማግኘት በተስፋ መውደቅ መቆም ምን ቢያለፋ ተስፋ ካለ ብርሃንማ ይወለዳል ከጨለማ አትሸበር በወጀቡ ተራራ ነው ጎበዝ ልቡ እልፍ ባለ ቁጥር እልፍ ያተርፋል ሰው በፍቅር ማለፊያ ሲል ነው ማለፊያ ሰው የማይድን ከሃሳብ ጥድፊያ ማለፊያ ሲል ነው ማለፊያ ሰው የማይድን ከሃሳብ ካፊያ ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ችግር ፈተናው (ያልፍል እንደ ጉም) ቢልም ጉም ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ያልፍል እንደ ጉም (ያልፍል እንደ ጉም) ችግር ፈተናው (ያልፍል እንደ ጉም) ቢልም ጉም ጉም (ያልፍል እንደ ጉም)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out