Lyrics

ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ ሰንዝሮ ማይመልስ ወርዶ ማይረታ በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወድያ ማዶ የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ (አቤት) ልክ እንደ ጀግና ሰው ምነኛ በረታው (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ምነኛ በረታው ምነኛ በረታው ጎጃም ተሻግሬ ጎብዝ ሆኜ መጣው (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ጀግና ሆኜ መጣው አንቺን ይዜ መጣው እንግዲያው ያውልሽ ውሰጂኝ ማርኪና (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ውሰጂኝ ማርኪና ውሰጂኝ ማርኪና እንደፈለክሽ አርጊኝ የበላይ ነሽና (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) የበላይ ነሽ እና የጎበዝ ነሽና ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማሬዋ ጋምዬ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ ደፋር አርጊው ልቤን እንደ በላይዬ ጋምዬ ጋሜዋ ወይ ደምዬ ውይ ደሜዋ እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ እውይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ ሁል ጊዜ ከፍ ብለሽ የምትቀጪ የበላይ ሆነሽ ነው የምትመረጪ በላይ የመረቀው ሀገሩን ነው መሰል ቢወለድ ጀግና ሰው የሚይስጠራ በድል የበላይ ፀባይ ይዘዋል ሰዎቹም ለፍቅር ነው እንጂ ለፀብ አይመቹም ምን ነካህ አትበሉኝ ማን ሊነካኝ ደርሶ ክንዴ ጎራዴውን ጀበርናውን ወርሶ ሰንዝሮ ማይመልስ ወርዶ ማይረታ በላይን ያለ ሰው ከታጠቀ አይፈታ እንግዲያው ማን ደፍሮኝ ይሞክረኝና የስመ ጥሩ ሰው የበላይ ነኝና ልቤ ፍቅር ሰራ አባይ ወድያ ማዶ የበላይዬን ዘር ጎጃሜዋን ወዶ ዙሪያ ዳር ድንበሩን አፈሩን ኩሩበት (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ሀገሩን ኩሩበት እንድትመኩበት እነ በላይ ናቸው የተወለዱበት (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) የተፈጠሩበት ታሪክ የሰሩበት ከእንግዲ ጎጃም ላይ ምን ተሰራ አትበሉ (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ምን ተሰራ አትበሉ ምን ተሰራ አትበሉ ታሪክ ጠይቃችው በላይ በላይ በሉ (ሆይ ሆይ) (ሆይ ሆይ) ጀግናው በላይ በሉ ጎበዝ ወዳድ ሁሉ ደሜዋ ድማሜዋ ደሜዋ ድማሜዋ አንቺ የጎጃም ጥንቅሽ እንዴት ነሽ ማሬዋ ጋምዬ ነይ ጋምዬ ጋምዬ ነይ ጋምዬ ደፋር አርጊው ልቤን እንደ በላይዬ ጋምዬ ጋሜዋ ጋምዬ ጋሜዋ እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ እሰይ ስበቤዋ እሰይ ድማሜዋ ሀይማኖተ ፅኑ ልበ ኩሩ ነሽ ከእነ በላይ ሀገር ጎጃም ተወልደሽ ኧረርዬ ርዬ ኧረርዬው መላ ጎጃም ተገበየ ፍቅር እና ተድላ እኚህ ጎጃሜዎች ልዩ ጣዕም አላቸው የንቦች እንጀራ ማር እያበሏቸው (አቤት ምቺና) (አቤት ምቺና) (አቤት ምቺና)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out