Lyrics

አላዝን አላዝን ግልፁን ልንገርሽ ወኔ አጥቼ አይደለም የታማሁብሽ ከንቱ ቢለፈልፍ ተናግሮ አናጋሪ የወደደ አይደለም የጠላ ነው ፈሪ ኧረ አይደለሁም አይደለሁም ደህና ደካማ ጎኔን በአንቺ አዩብኝና ስሜ ላይ ሄዱ ጎዝጉዘው እንደሳር የወደቀ ዛፍ መቼ ያጠዋል ምሳር ቀን የሰጠው ለታ ቅል ድንጋዩን ሰብሮ ወትሮስ እንደ ጀግና ያውቃል ወይ ፎክሮ አገኘሺኝ እንጂ ድንገት ስዘናጋ ባልቆጨኝ ለፍቅርሽ የከፈልኩት ዋጋ ሳስበው ሳሰበው ገባኝ ሳዳምጠው ውስጤን ሽንፈት አልለውም በቃ በአንቺ መበለጤን እንኳን ሰው ደካማዉ ቀርቶ የፈጠረው ጌታ ተስሞ ተሸጧል በወዳጁ ማታ ፍቅርን ብዬ እንጂ የምተናነሰው ከመረረማ በእኔ ሚብሰው ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ አላዝን አላዝን ግልፁን ልንገርሽ ወኔ አጥቼ አይደለም የታማሁብሽ ከንቱ ቢለፈልፍ ተናግሮ አናጋሪ የወደደ አይደለም የጠላ ነው ፈሪ ኧረ አይደለሁም አይደለሁም ደህና ደካማ ጎኔን በአንቺ አዩብኝና ስሜ ላይ ሄዱ ጎዝጉዘው እንደሳር የወደቀ ዛፍ መቼ ያጠዋል ምሳር ባልጨክን ነው እንጂ ፊቱን በአንቺ ጉዳይ ቤቴን ባልጎበኘው አሳስቆ ገዳይ ወዶ መለየትን ቢመርም ልቅመሰው ከእንግዲህ ውለታን አልጠብቅም ከሰው ብቻ ቀርቦ ጉርሻ ልምዱም ባልኩራራበትም ሰው ራቀኝ ብሎ መቼም እጅ አፉን አይስትም ለምን ስል ልከፋ ደሞ ልዘን ምን በወጣኝ አንድ አንቺን ነው እንጂ ሀቄን አያሳጣኝ ፍቅርን ብዬ እንጂ የምተናነሰው ከመረረማ በእኔ ሚብሰው ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ ጀግና የጀግና ጀግና ልቤ ቆራጡ ዘበት ነው አንቺን መለማመጡ
Writer(s): Samuel Alemu, Mastewal Eyayu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out