Lyrics

ያለ ነበር በዚህ መደሰት መከፋት የሚኖር ነው ነገም ካሉ መውደቅ መነሳት አንድም ሰው ለማግኘት አንድም ሰው ለማጣት ለማጣት መንገድ አይደለም ወይ የመሄድ የመምጣት የመምጣት ስለይሽ የኔ ሰው ያልኩሽን ከጎኔ በጊዜው መንገድሽ ሳይገባኝ ኖሬያለሁኝ እኔ የኖሩት ሲያልፍ ይሆን የለም ወይ ትዝታ ነገሩን እስኪ እናንሳው ዛሬ እንዲያው ለጨዋታ አጋርሽ መሆኑን ሰምቼ ያ የጥንት ወዳጅሽ ወዳጄ እቴ ሙች ግራ ነው የገባኝ ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ ባይ እስኪ ግለጪልኝ ይሄን ነገር ይሄን ነገር ያ ሰው የዚያን ጊዜ ምንሽ ነበር ምንሽ ነበር ኧረ እየው ድማሙ ኧረ እየው ድማሙ አሁን ምን ይሉታል ይህ አይነት ጨዋታ ትተኸው የለም ወይ አንተው ያንተን ፋንታ (ጉብልዬ) አንተ ጉብልዬ (ጉብልዬ) አንተ ጉብልዬ (ጉብልዬ) አይተኸው በሌላ (ጉብልዬ) ባይገባህ ነው እንጂ (ጉብልዬ) እርቅ አላሚ ነበር የአንተማ ወዳጅ (ጉብልዬ) ወጉማ አጎንብሶ (ጉብልዬ) ለምስጋና ነበር አናከሰው ስንቱን አወይ የሰው ነገር (ጉብልዬ) ጥለው ባያነሱም (ጉብልዬ) የተዉትን ነገር (ጉብልዬ) ዞረው ባያዩትም (ጉብልዬ) የራቁትን ሀገር (ጉብልዬ) እውነታ ቢሆንም (ጉብልዬ) ዛሬን መስሎ ማደር (ጉብልዬ) አይከፋም አንዳንዴ (ጉብልዬ) ትላንትን መጠርጠር (ጉብልዬ) አብረሽኝ እያለሽ (ጉብልዬ) የነበረው ባዳ (ጉብልዬ) መች ይሆን ተዛምዶሽ (ጉብልዬ) ያረገኝ እንግዳ ትላንት እንግዳዬ የነበረው ጎብኚ ትላንት እንግዳዬ የነበረው ጎብኚ ይኸው ዛሬ ደሞ እኔ እንግዳው ነኝ አሂሂሂሂ ኧረ እየው ድማሙ ኧረ እየው ድማሙ ኧረ እየው ድማሙ ኧረ እንደው ድማሙ እንዴት ባልዋለበት ሰው ይጠፋል ስሙ አሄሄ እንደተድላው ጊዜ እንደደስታው ቀን እንደተድላው ጊዜ እንደደስታው ቀን ሰው ከሰው ይውላል መቼም በሃዘን አሄሄ አባባይ ሆንኩ እንጂ ላጎደልከው ደስታ አባባይ ሆንኩ እንጂ ላጎደልከው ደስታ እኔስ አልመኝም የወዳጄን ቦታ አሄሄሄ አለምዬ አለምዬ አለም ሸጋ ቁጭ ብለን እናውጋ አለምዬ አለም ሸጋ ቁጭ ብለን እናውጋ አሄሄ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out