Lyrics

ዓይኔማ አሀሀ አይፈልገው ካንቺ አልፎ ማየትን አካሌም አይታክተው አብሮሽ መቆየትን ውዴ ውዴ የኔው ነሽ ስሜቴ በዓይን የሚገባሽ ውዴ ውዴ የኔው ነሽ ጨዋታ በዓይን የሚገባሽ ወሰን አልባው ፍቅርሽ ጠብቆኝ በስስት አድርጎኛልና መንገዴን እንዳልስት ላንኳኳለት ሁሉ ልቤ አይከፈትም እንኳንስ አካሌ ሃሳቤ አይሸፍትም የልቤ ንግሥት አድርጌሻለሁ ውዴ እልሻለሁ ውዴ ውዴ ካንቺ ርቆ አይችልም ሆዴ ውዴ ውዴ የማልጠግብሽ ሆነሻል እንዴ ውዴ ውዴ ባንቺ ፍቅር ሰክኗል መውደዴ ውዴ ውዴ እስትንፋሴ ሆነሻል አንዴ ዓይኔማ አሀሀ አይፈልገው ካንቺ አልፎ ማየትን አካሌም አይታክተው አብሮሽ መቆየትን ውዴ ውዴ የኔው ነሽ ስሜቴ በዓይን የሚገባሽ ውዴ ውዴ የኔው ነሽ ጨዋታ በዓይን የሚገባሽ ተፈጥሮ ነውና ይነጋል ይመሻል ዓይኔ ግን በስስት ጨፍኖም ያይሻል ከፀጉርሽ ቅንጣት አንዲቷም ዘለላ ስትወድቅ አያሳየኝ ይከፋኛልና ከጎኔ ቁሚ እስከ እድሜዬ አመሻሽ ክፉ ሳይነካሽ ውዴ ውዴ ካንቺ ርቆ አይችልም ሆዴ ውዴ ውዴ የማልጠግብሽ ሆነሻል እንዴ ውዴ ውዴ ባንቺ ፍቅር ሰክኗል መውደዴ ውዴ ውዴ እስትንፋሴ ሆነሻል አንዴ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out