Lyrics

የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የኔው ነሽ የኔ ብቻ አይደለሽም የሌላ ቃልኪዳን ገባሁልሽ ላልከዳሽ በመሀላ በእኔ ሰላምሽ ይብዛ ያኩራሽ ላንቺ ማደሬ አስደስቼሽ ልደሰት አለኝታዬ ነሽ ፍቅሬ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የፍቅር ማጣፈጫ ቅመም አለው ጨዋታሽ ሳቅ ስትይ ካላየሁ አልደምቅም በዝምታሽ አጥቼስ ውዬ ሳድር አይረጋልኝም ልቤ ጭር እላላሁ ያላንቺ አትራቂ ካጠገቤ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ ኮከባችን ገጥሞልን አጣምሮን እጣ ፋንታ ስሜትን ያጋራናል ፍቅራችን እንደመንታ ከታመምሽም መታመም ደስ ሲልሽ ደስታዬ የሆንሽውን ለመሆን ልብሽ ላይ ነው ቦታዬ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ የኔ ፍቅር የግሌ ነሽ ሳቅ በይ አንዴ ልይሽ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out