Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Bisrat Surafel
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Bisrat Surafel
Songwriter
Bewketu Seyum
Lyrics
Frezer Taye
Arranger
PRODUCTION & ENGINEERING
Bisrat Surafel
Producer
Lyrics
እኔ ጥቁሬ ብስሬ ሆይ
አንድ አንኳር ጨዋታ
ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ
ዙሪያው በራ ስትስቂ
ለውበትሽ ምን ይደገስ
ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ
ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ
ዙሪያው በራ ስትስቂ
ለውበትሽ ምን ይደገስ
ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ
ልብሽ እና ቀልብሽ ከሰማይ ሲርቅ
ምን ሆኜ ልገለጥ ባይንሽ እንድደምቅ
ላገኛት ነው እያልኩ ዋልኩኝ በሰመመን
አግኝቼ እስከማቅፍሽ የቀን ህልሜን ልመን
(እና) ባይንሽ ላልሞላ
(እና) በጌጥ በልብሴ
(እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ
(እና) ተጋረደብኝ
(እና) መላና ዘዴ
(እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ
በአንድ እጇ አምባር አላት
በአንድ እጇ የላትም
እንደንጉሥ ሀገር ሰው አይለያትም
ወንዙ ሞልቶ ቢፈስ እሷ ምን ቸገራት
(እና) ወዳጇ ብዙ ነው ወድቆ ሚያሻግራት
ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ
ዙሪያው በራ ስትስቂ
ለውበትሽ ምን ይደገስ
ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ
ኮኮቤ ነሽ ሌት አድማቂ
ዙሪያው በራ ስትስቂ
ለውበትሽ ምን ይደገስ
ምን አድርጌ ባይንሽ ልንገስ
ባ'ገር በመንደሬ ሚታገለኝ የለም
ማንን ልርታ ይሆን በ'ጅሽ እንድሸለም
የኑሮዬን ጣጣ በፍቅርሽ ረሳሁ
አስቤሽ ተኝቼ ደስ ብሎኝ ተነሳሁ
(እና) ባይንሽ ላልሞላ
(እና) በጌጥ በልብሴ
(እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ
(እና) ተጋረደብኝ
(እና) መላና ዘዴ
(እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ
በአንድ እጇ አምባር አላት
በአንድ እጇ የላትም
እንደ ንጉሥ ሀገር ሰው አይለያትም
ወንዙ ሞልቶ ቢፈስ እሷ ምን ቸገራት
(እና) ወዳጇ ብዙ ነው ወድቆ ሚያሻግራት
አለ አንኳር ጨዋታ
አለ አንኳር ጨዋታ
ሲካሱ በመውደድ
የማታ የማታ
አለ አንኳር ጨዋታ
አለ አንኳር ጨዋታ
ሲካሱ በመውደድ
የማታ የማታ
(እና) ባይንሽ ላልሞላ
(እና) በጌጥ በልብሴ
(እና) አስሬ ደጅሽ መመላለሴ
(እና) ተጋረደብኝ
(እና) መላና ዘዴ
(እና) አንቺን አፍቅሬ ሞኝ ሆንኩኝ እንዴ
እና
Lyrics powered by www.musixmatch.com