Music Video

Tshaye Yohannes – Yeneta - ጸሐዬ ዮሐንስ - ላንቺማ - - Ethiopian Music
Watch {trackName} music video by {artistName}

Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Tsehaye Yohannes
Tsehaye Yohannes
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Fird Yawikal Nigussie
Fird Yawikal Nigussie
Songwriter

Lyrics

ይመስገን ይመስገን ይህ አይኔ ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ የዉበትሽ ጮራ ጭጋጉን ጠረገዉ ቤቴን አደመቀዉ ህልሜን አተለቀዉ ሙሉ ሴትነትሽ ኩድለቴን ሸፈነዉ የፍቅርሽ ይዘቱ ህይወቴን ለወጠዉ በአለም አይገኝም አንቺን የሚመስል ዴዝዴሞናም ታሪክ ሞናሊዛም ስዕል አቻ የለሽ አንቺ ሚዛን ምንነቴ አምላክ የሰራሽ ወስዶ ከአጥንቴ ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ ለአንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ ይመስገን ይመስገን ይህ አይኔ ፈገግታሽን አይቶ የኔ አለም ብሩህ ሆነ ቀኔ ዉበትሽን አይቶ የኔ አለም ዘረፈልኝ ቅኔ ይመስገን ይመስገን ሀሳቤ ስለአንቺ ተጠቦ የኔ አለም አደብ ገዛ ቀልቤ ስለአንቺ ተጨንቆ አለሜ ፍቅር ገባ ልቤ እንዳይረግፍ እሻለዉ የዉበትሽ ጤዛ ለማማር መድመቅሽ እሆናለዉ ቤዛ በጭንቀት ባይስላት ትላንት ሞናሊዛን ዛሬ አትደፋም ነበር የዉበት አክሊሏን ሙሉ ሴትነትሽን ዘዉትር አስባለዉ ለደስታ ሰላምሽ እንቅልፌን አጣለዉ እድሜ ፀጋ ሰቶሽ ኑሪ ለአለም አንቺ እኔ ካህን ሆኜሽ እኖራለሁ ለአንቺ ላንቺማ መለከት ይነፋ ላንቺማ በይፋ ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ላንቺማ አጊጣ ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ ላንቺማ መለከት ይነፋ ለአንቺማ በይፋ ላንቺማ ነጋሪት ይመታ ሚስጥር የሚፈታ ላንቺማ ጨረቃዋ ትዉጣ ለአንቺማ አጊጣ ላንቺማ ዉበትሽን አይታ ትድመቅ በፈገግታ ላንቺማ ላንቺማ አጊጣ ላንቺማ ትድመቅ በፈገግታ
Writer(s): Elias Woldemariam, Fird Yawikal Nigussie Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out