Lyrics

ጎጆ ልወጣ ነዉ መደብ ላደላድል እድሜዬ ጨመረ ብቸኝነት ስጥል ቤቱ ተዋቀረ ምሶሶዉ ተሰራ እስቲ ባት አሳቅሉኝ ይሁን የኔ ተራ ጎጆ ልወጣ ነዉ መደብ ላደላድል እድሜዬ ጨመረ ብቸኝነት ስጥል ቤቱ ተዋቀረ ምሶሶዉ ተሰራ እስቲ ባት አሳቅሉኝ ይሁን የኔ ተራ ሀገሬዉ ተቸገር ና ታዛዬን ስራ የኔማ አዲስ ጎጆ በደቦ ይሰራ ወንበሩ ፀበሉ መንደሩም ይነሳ ያደግንበት ባህል ወጉ እንዳይረሳ የቤቴ ዉጋግራ ድምድሙ ተሰርቶ ባቱም ተበጅቷል የሚከድነዉ አቶ መሰረት ተጥሎ ምሶሶ ከቆመ ባት መስቀል ብቻ ነዉ እድሜ ከጨመረ የአያት የቅድመ አያት ባት ነዉና ወጉ በኔም አዲስ ጎጆ እንቦሶች ይደጉ አባቴ መርቀኝ ለዚህ በቃሁ ዛሬ እትብቴ ካለበት ቤት ልስራ ከሀገሬ የቤቴ ዉጋግራ ድምድሙ ተሰርቶ ባቱም ተበጅቷል የሚከድነዉ አቶ መሰረት ተጥሎ ምሶሶ ከቆመ ባት መስቀል ብቻ ነዉ እድሜ ከጨመረ ቤቴን ስሩ እስቲ ቤቴን ስሩ ባት አሳቅሉኝ እስቲ ቤቴን ስሩ አማረብኝ ሆ ይበል ሀገሩ ቤቴን ስሩ እስቲ ቤቴን ስሩ ባት አሳቅሉኝ እስቲ ቤቴን ስሩ አማረብኝ ሆ ይበል ሀገሩ ጎጆ ልወጣ ነዉ መደብ ላደላድል እድሜዬ ጨመረ ብቸኝነት ስጥል ቤቱ ተዋቀረ ምሶሶዉ ተሰራ እስቲ ባት አሳቅሉኝ ይሁን የኔ ተራ ጎጆ ልወጣ ነዉ መደብ ላደላድል እድሜዬ ጨመረ ብቸኝነት ስጥል ቤቱ ተዋቀረ ምሶሶዉ ተሰራ እስቲ ባት አሳቅሉኝ ይሁን የኔ ተራ ይለቅለቅ ወለሉ ይመር ባኞማዳዉ ሳንቃዉን ማቀፊያ ጉበን ነዉ ይጠረግ መሰረቴ እንዲሆን የእትብቴ መነሻ ህይወቴ ካልቸረ እስከመጨረሻ ኩራዙም ከግርግም ይቀመጥ ዉበት ነዉ አእዋፉም ይሰቀል የቤት ግርማ ነዉ ዠንዲና መሰግያ ይወረድ ከመደቡ ቤት ለእንቦሳ በሉ ከአዳራሹ ግቡ መጋል እና ቡሬ እንቦሳ ይዉለዱ ባዋቀርኩት ጎጆ መንጋዎች ይዉለዱ ብላችሁ መርቁኝ አባቶች ትፉና የአለም ይሁን በሉኝ ይጠቅመኛልና ኩራዙም ከግርግም ይቀመጥ ዉበት ነዉ አእዋፉም ይሰቀል የቤት ግርማ ነዉ ዠንዲና መሰግያ ይወረድ ከመደቡ ቤት ለእንቦሳ በሉ ከአዳራሹ ግቡ ቤቴን ስሩ እስቲ ቤቴን ስሩ ባት አሳቅሉኝ እስቲ ቤቴን ስሩ አማረብኝ ሆ ይበል ሀገሩ ቤቴን ስሩ እስቲ ቤቴን ስሩ ባት አሳቅሉኝ እስቲ ቤቴን ስሩ አማረብኝ ሆ ይበል ሀገሩ
Writer(s): Elias Woldemariam, Abrishe Zeget Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out