Lyrics

ስጠብቅሽ ኖሬ ኖሬ ስናፍቅሽ ኖሬ ኖሬ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ስለተገናኘን ዛሬ ታጋሽ ሆኖ በመገኘት ቃል አክብሮ በመገኘት እንዴት እኮ ደስ እንደሚል ተለያይቶ መገናኘት የሩቅ ለሩቅ ፍቅር ያ ማይቻል ነገር ብታምኝም ባታምኝም ወፈፍ አርጎኝ ነበር መደንዘዝ አብዝቼ ከሰው አልጣጣም ይቺን ዕለት ነበረ ምናፍቃት በጣም በይ አይን አይንሽን ልየው አትለይ ከጎኔ ዛሬ ነው ቀናችን ፍቅር አንቺና እኔ ታግሶ ለቆየ ድሉ እራሱ ይደላል የተለያየ ሰው ሲገናኝ ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል እንኳን ባይኔ አየሁሽ ላመታት ናፍቄ ባካል አገኘሁሽ ደስ ይላል ደስ ይላል ዛሬ ተገናኘን እንኳንም አልቀረን እንደተለያየን ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል ስጠብቅሽ ኖሬ ኖሬ ስናፍቅሽ ኖሬ ኖሬ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል ስለተገናኘን ዛሬ ታጋሽ ሆኖ በመገኘት ቃል አክብሮ በመገኘት እንዴት እኮ ደስ እንደሚል ተለያይቶ መገናኘት ያንን ሁሉ ዘመን ያንን ሁሉ ማታ እንደ እብድ ሆኜ ነበር ባንቺ ሃሳብ ትዝታ በማያልቀው ፍቅርሽ ስጎዳ ስቸገር እንኳን አለፈ እንጂ ኑሮስ ከባድ ነበር በይ አይን አይንሽን ልየው አትለይ ከጎኔ ዛሬ ነው ቀናችን ፍቅር አንቺና እኔ ቃሉን ላከበረ ፍቅር ብዙ ይከፍላል የተለያየ ሰው ሲገናኝ ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል እንኳን ባይኔ አየሁሽ ላመታት ናፍቄ ባካል አገኘሁሽ ደስ ይላል ደስ ይላል ዛሬ ተገናኘን እንኳንም አልቀረን እንደተለያየን ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል ደስ ይላል እንዴት ደስ ይላል እንዴት ደስ ይላል ተለያይቶ መገናኘት እንዴት ደስ ይላል
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out