Listen to Asina Genaye (feat. Stif Lion, Jahphate, Beferdu, Ezra, Kuki & Haileab) by Ahadu

Asina Genaye (feat. Stif Lion, Jahphate, Beferdu, Ezra, Kuki & Haileab)

Ahadu

Hip-Hop/Rap

2,831 Shazams

Lyrics

አሐዱ አብዬም ተነሱ በሉን የጌቶቹ ጌታ በረከት የሆኑኝ ፍቅር የማታ ማታ ጎዶሎ የማያውቁ ደግሞ ሁሌም ጎተራቸው ስንቱን ያጠገበው ደግሞ ሙሉ መሶባቸው ከሸራ አልፎ ሙላቱ ከስንዴ ክምሩ መቼም ላይጎላቸው ሙሉ ነው መንደሩ እምዬም ብቅ በይ ደግሞ ካገር ጥበብሽ የእጅ ወርቅሽ ያጎላው ደግሞ ያምራል ጥለትሽ ሸብ ያለው መቀነቱ ከወገብሽ ያለው ሁሉን ቻይ አንጀትሽ ስንቱን የሚችለው አውዳመቱ ደርሶ ሲባል አሲና ገናዬ ደጅሽ እመጣለው ደግሞ ጠብቂኝ ሸግዬ አሲና በል አሲና ገናዬ ኢዮሃ አሲና በል ኢዮሃ አሲና ገናዬ አሲና በል በገና ጨዋታ ኢዮሃ አሲና በል ኢዮሃ አሲና ገናዬ አለን ውብ ባህል 'ሚበቃ ለዓለም የማይል ዘር ቀለም መጥተዋል አዎ ወደው የአውዳመቱን ድባብ ፈዘው ነው የሚያዩ ሀብታም ደሃ ፈቅዶ ሲረዳዳ ደጁ ሁሌ ቅን ዘመድ ይምጣ ባዳ ጠላውም ቀርቧል ጠጁም ከገበታ ዶሮ በጉ ሁሉ የጣዕሙ ትዝታ በዓል በዓል የላል ይሸታል መንደሩም ሰላም ያኮራል መጫወት ካገር ልጅ ጋር ደስ ይላል ወተናል ወርደናል አጥተን አግኝተን ተመስገን ብለን ይኸው ለዛሬ ቀን ደርሰናል እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አብሮ አደረሰን እንዲሁ እንዳገናኝን ካመት ዓመት አይለየን አሲና በል ገናዬ አሲና በል እንበል አሲና በል አሲና ገናዬ ከናት ካባቴ ቤት ያለኝ ትዝታ እኅት ወንድሞቼ ደስ የሚል ጨዋታ ጠራኝ የጠዋቱ ጤዛ የበረቱ ሽታ የእምዬ ጉድ ጉድ የአባብዬ ደስታ ያለንን ተካፍለን በፍፁም ቅንነት ዘመድ አዝማዱም ሁሉም በያለበት ሲያከብረው ይኖራል በሚያምር ኅብረዜማ በአባቶቻችን ቃል እያልን እዮሃ (እልልልል) አሲና በል አሲና ገናዬ ኢዮሃ አሲና በል ኢዮሃ አሲና ገናዬ አሲና በል በገና ጨዋታ ኢዮሃ አሲና በል ኢዮሃ አሲና ገናዬ ኢዮሃ ኢዮሃ ኢዮሃ ኢዮሃ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out