Lyrics

በተሳልኩት ስለት ካልወጣሁ ከማፍቀር ከማፍቀር ከማፍቀር እኔማ ከማፍቀር ስረሳ ካላየሁ ከሃሳቤ ስትቀር ስትቀር ስትቀር የኔ ዓለም ስትቀር ምን ብዬ አነግሣለሁ ከእንግዲህ ታቦቱን ታቦቱን ታቦቱን እኔማ ታቦቱን ባንተ ለመጨከን ካልሰጠኝ ሐሞቱን ሐሞቱን ሐሞቱን ጌታዬ ሐሞቱን በሆነለት በሆነለት ልቤ መርሳት በሆነለት በሆነለት በሆነለት አንተን መተው በሆነለት ድንኳን ቢቸግረኝ ባጣ እንኳን ማደሪያ አላውቅም ቀርቼ እኔ ጽዮን ማርያም በጠዋቱ ገዳም ግሸን ተሻግሬ ምላሽ አልነበረም የልቤን ነግሬ ዛሬ ካንተ ርቄ ብሳል በነጠላ ጠፋ ሰሚ ታቦት ወዶ ለሚጠላ በእንጦጦዋ ብልህ በኪዳነምሕረት ተወው በእመቤቴ ይሄን ደርሶ መቅረት ተወው በእመቤቴ ይሄን ደርሶ መቅረት ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ በተሳልኩት ስለት ካልወጣሁ ከማፍቀር ከማፍቀር ከማፍቀር እኔማ ከማፍቀር ስረሳ ካላየሁ ከሃሳቤ ስትቀር ስትቀር ስትቀር የኔ ዓለም ስትቀር ምን ብዬ አነግሣለሁ ከእንግዲህ ታቦቱን ታቦቱን ታቦቱን እኔማ ታቦቱን ባንተ ለመጨከን ካልሰጠኝ ሐሞቱን ሐሞቱን ሐሞቱን ጌታዬ ሐሞቱን በሆነለት በሆነለት ልቤ መርሳት በሆነለት በሆነለት በሆነለት አንተን መተው በሆነለት በአቦ በሥላሴ በገብርኤል ብዬ አልሰማ ብትለኝ ተጓዝኩ እኔስ ጥዬ ለነፍሴ ለማደር ምንኩስናን ብሻ በእኔ መንኚ አለኝ ፍቅርህ እንደ ዋሻ ዓለም በቃኝ ብዬ ገና ቆቤን ሳልጭን ዐይኖችህ ይሉኛል እገዳምሽ አምጪን እነሱን አልመን አይተው ያልጠገቡ ለነፍስ ያድራሉ ወይ ከገዳም ቢገቡ ለነፍስ ያድራሉ ወይ ከገዳም ቢገቡ አንተማ ላመልህ እበተስኪያኑ ውለህ ትሳላለህ አሉኝ ጥላ አመጣ ብለህ ጧፉ ሲወረወር እጣን ሲዘረገፍ ምነው ባላሳየኝ እኔስ ያንተን መርገፍ ምነው ባላሳየኝ እኔስ ያንተን መርገፍ ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ ባስረሳኝ አንተንስ ባስረሳኝ ባስረሳኝ ጌታዬ ባስረሳኝ ባስረሳ ባስረሳኝ ባስረሳ ባስረሳኝ ባስረሳ ባስረሳኝ ባስረሳ ባስረሳኝ
Writer(s): Bisat Seyoum Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out