Lyrics

ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ አመል ያለብኝ እኔ ሱሰኛሽ አይቼሽ አልጠግብ ውጬ አልጨርስሽ መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው መውደድሽ ግሎ ልቤን ተኮሰው እኔስ የት ልግባ ወዴት ልድረሰው የፍቅርሽ ብዛት ልቤ ውስጥ ገብቶ አርበተበተኝ አንጀቴን በልቶ እኔ ሱሰኛሽ ላሞጋግስሽ እንደ ዳዊቴም እስኪ ልድገምሽ የፍቅርሽ ብዛት ልቤ ውስጥ ገብቶ አርበተበተኝ አንጀቴን በልቶ እኔ ሱሰኛሽ ላሞጋግስሽ እንደ ዳዊቴም እስኪ ልድገምሽ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ እና ሐሙስ አርብ ዓመት ሆነ ቀናቱ እስኪደርስ ሱስ ያለኝ እኔን መች ያስችለኛል ሲመሽ ሲነጋ አንቺን ይለኛል ሱስ ያለኝ እኔን መች ያስችለኛል ሲመሽ ሲነጋ አንቺን ይለኛል እንዳንፀባራቂ ፊትሽ ሲያበራ መቃው አንገትሽ ከሩቅ ሲጣራ ተልፈሰፈስኩኝ ጉልበት አነሰኝ ልቤ ተነካ መቻል አቃተኝ እንዳንፀባራቂ ፊትሽ ሲያበራ መቃው አንገትሽ ከሩቅ ሲጣራ ተልፈሰፈስኩኝ ጉልበት አነሰኝ ልቤ ተነካ መቻል አቃተኝ አላስቀድስም ታቦት አላነግሥ የኔ ውዳሴ አንቺ የኔ መቅደስ ሱባዔ አልገባ መቆሚያም የለኝ ምርኩዜም አንቺ እስኪ አንቺው ባርኪኝ ሱባዔ አልገባ መቆሚያም የለኝ ምርኩዜም አንቺ እስኪ አንቺው ባርኪኝ ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ ጨረቃዋ ስትደምቅ ከዋክብት ሲወጡ ድምጽሽ ይነፍሳል ከዛፍ ከቋጡ ሰማይ ሲላወስ ደመና ሲለብስ ብርሃን ሲጠፋ ጨለማ ሲደርስ
Writer(s): Teshome Mitiku Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out