Lyrics

ምስቅልቅል ሕይወቴ ሕይወቴ በፍቅርሽ አማረ የስኬቴ መንገድ ጎዳና ባንቺ ተጀመረ አነሳሁሽ በደግ በደግ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ አነሳሁሽ በደግ በደግ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ የጥሩ አፍቃሪ ናሙና የውስጤም ብርታት ነሽና አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ ሕይወቴ ሠምሮ እንዲቃና ከእኔ እኩል ለፍተሻልና አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ ተመስገን ስለው ጠዋት ማታ አልረሳም ያንቺን ውለታ አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ምስቅልቅል ሕይወቴ ሕይወቴ በፍቅርሽ አማረ የስኬቴ መንገድ ጎዳና ባንቺ ተጀመረ አነሳሁሽ በደግ በደግ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ አነሳሁሽ በደግ በደግ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ በፍቅርሽ ዓይኔን ገለጥኩኝ በቃ አሁን መኖር ጀመርኩኝ አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ ሰው ሆነሽ ሰው አደረግሺኝ ዓይኔንም በዓይኔ አሳየሺኝ አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ ኑሮዬን እየተጋራሽ በውስጤ ሰላም የዘራሽ አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ብሌኔ ብሌኔ የማይሽ እንደ ዓይኔ ብሌኔ ብሌኔ ብርሃኔ ነሽ ለኔ ብሌኔ ብሌኔ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out