Lyrics

የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ ስትከተላት በልጣብህ ከኔ ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ ስትከተላት በልጣብህ ከኔ ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ ይገርመኛል እኔ የአንተ ማንገራገር ጊዜህ ሲጠፋ ባበቃ ነገር ወይ አላወክበት ሰዶ ማሳደዱን ከራስህ ጥፋት የመጣዉን ጦስ በል ቻለዉ መንገዱን ምነዉ በቀደምካት ያን ጊዜ ሳትቀድምህ ሰላም ሳታጣ እንዲህ ሳያምህ የእሷን ሳትቀበል የአንተን ማን ስጥ አለህ እንደ ጥፋትህ ቅጣትህ ቀሏል ልቤ እድለኛ ነህ እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ ጭንቀት ሀዘን አንግዛ ያ ፍቅሯን ላታገኝ የማይሆን ስትመኝ እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ ስትከተላት በልጣብህ ከኔ ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ ከጅምሩ ነበር እሳትን በቅጠል ዉስጥ ዉስጡን ነዶ ሳይቀጣጠል የወደደ እራሱን ይጐዳል ቢባልም ልቤ የአንተ ግን ራስን መጣል ነዉ ፍቅር አይባልም የትርታዬ ዋስ ልቤ ዋስትናህ ዘመድህ እኔ ሰላም ጤናህ ለምን አተዋትም እንደሷ ወስነህ ያለፈን ስትል ጊዜ ቢያልፍብህ ተጐጂዉ አንተ ነህ እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ ጭንቀት ሀዘን አንግዛ ያ ፍቅሯን ላታገኝ የማይሆን ስትመኝ እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ ጭንቀት ሀዘን አንግዛ ያ ፍቅሯን ላታገኝ የማይሆን ስትመኝ እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out